በፊሊፔንስ እየተካሄደ ባለው ‹‹ሚስ ሱፐር ሞዴል ወርልድ ዋይድ›› ውድድር ላይ ሩት ይርጋለም ለመጨረሻው ውድድር ከቀረቡ 11 ቆነጃጅት አንዷ መሆኗን ተነግሯል፡፡
ይህ ውድድር ሊጠናቀቅ 2 ቀናት የቀሩት ሲሆን ዛሬ ሁሉም ተወዳዳሪዎች በአገራቸው ባህላዊ ልብስ ፎቶ የመነሳት ስነስርአት አከናውነዋል፡፡
እንዲሁም የፋሽን ሾው ትርኢት አሳይተዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ የውድድሩ አንድ አካል ሲሆኑ ተወዳዳሪዎቹ በማኒላ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችንም ጎብኝተዋል፡፡
የመጨረሻው ውድድር ከ2 ቀናት በኋላ ጁን 26 በማኒላ በሚገኘው ኦኮዳ ሆቴል ግራንድ ቦል ሩም ይከናወናል፡፡ ኢትዮጵያን ለወከለችው ሩት በድጋሚ መልካም እድል ተመኝተናል፡፡
