ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት በተመድ መንበር ላይ ተሰይሟል

Date:

ከኒውክሌር ጦር መሳሪያ በላይ ዓለምን እያስፈራት ያለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ጉዳይ፣ ዛሬ በአንድ ስመ-ጥር ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት እጅ ላይ ወድቋል።

ይህ ወጣት አዕምሮ፣ ከሀርቫርድ እስከ ኦክስፎርድ፣ ከማይክሮሶፍት እስከ IBM የጥበብ ማማዎች ላይ ተራምዶ፣ ዛሬ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) መንበር ላይ ተሰይሟል!

የሳይንሱ ኮከብ ጉዞ
•  የማይክሮሶፍት ኩራት፦ በ “AI for Good” ላቦራቶሪ ውስጥ ዓለምን የሚለውጡ ምርምሮችን ሲመራ ቆይቷል።
•  የኦክስፎርድና ሀርቫርድ አሻራ፦ ማሽኖች ለሰው ልጅ ጤና እንዴት እንደሚሠሩ በሚያስደምም ጥልቀት የመረመረ ባለሙያ።
•  የዕውቀት ጎተራ፦ ከ27 በላይ ዓለም አቀፍ የሳይንስ ምርምሮችን ለዓለም ያበረከተ የዘመኑ ጥቁር አልማዝ።

የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአውሮፓውያኑ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ባስተላለፉት ታሪካዊ ውሳኔ፣ ዶ/ር ግርማው ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ 40 ታዋቂ ምሁራንን እንዲመራና እንዲያስተባብር በይፋ ሾመውታል።


“ኢትዮጵያ በዲጂታል 2030 ጉዞዋ ላይ ሳለች፣ እንዲህ ያለውን ‘ባለምጡቅ አዕምሮ’ ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ መላኳ ለሀገር ትልቅ ኩራትና ለቀጣዩ ትውልድ ደግሞ ተስፋ ነው!”


ግርማው አበበ (ዶ/ር) በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት፣ ይህን አስፈሪ የተባለለትን ቴክኖሎጂ ለሰው ልጅ ሰላምና እድገት እንዲውል በማድረግ ረገድ የዓለምን መሪ ሚና ይጫወታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...