«ኢትዮጵያ ከጦርነትና ከስደት የምታርፍበት ዘመን ይሁን!»

Date:

የኢትዮጵያ የዘውድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ልዑል ኤርሚያስ ሣህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ፣ ለ፳፻፲፱ ዘመነ ሉቃስ አዲስ ዓመት ባስተላለፉት መልእክት፥ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮያውያን አዲሱን ዘመን በተስፋ እንዲቀበሉ ጥሪ አቀረቡ።

ልዑሉ በእንቁጣጣሽ በዓል ምኞታቸው ላይ እንደገለጹት፥ በዓሉ ከንግሥተ ሳባ ዘመን ጀምሮ የመጣ የኢትዮጵያውያን ልዩ ኩራትና ባህል ነው።

ስለዚህም ያለፈውን ዓመት የደስታና የሐዘን አጋጣሚዎች በማሰብ፣ ይህንን ታላቅ ባህል ያቆዩልንን አባቶችና እናቶች እንዲሁም ፈጣሪን ማመስገን እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተጨማሪም በሀገራችን ላለፉት በርካታ ዓመታት የቆየው ጦርነት፣ መከፋፈልና ችግር ህዝባችንን ለእንባና ለስደት መዳረጉን ያወሱት ልዑል ኤርሚያስ፥ አዲሱ ዓመት ይህ መከራ የሚያበቃበት የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት ዘመን እንዲሆን መጸለይ እንደሚገባ ገልጸዋል።

አሁን ባለው የዓለም አቀፍ ችግርና የኑሮ ውድነት ምክንያት ህዝባችን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ በመጠቆም፥ እያንዳንዱ ሰው ከእርሱ በባሰ ሁኔታ ላይ ያሉ ወገኖቹን በቁሳቁስ፣ በሐሳብና በጸሎት እንዲረዳ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ፳፻፲፱ ዘመነ ሉቃስ ለኢትዮጵያና ለልጆቿ የሰላም፣ የጤናና የመታደስ ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...