ኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል

Date:

ኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ።

ስለኢትዮጵያ ሁለተኛው ምዕራፍ 20ኛው መድረክ መሰረት ልማት ስለ ኢትዮጵያ በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በመድረኩ ባቀረቡት የመነሻ ጽሁፍ እንደገለጹት፤ ኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

በኢትዮጵያ ከ100 ሰዎች 76ቱ የኢንተርኔት አገልግሎት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ የገለጹት ኃላፊዋ፤ ለኢትዮጵያ 8 ነጥብ 5 ለጂዲፒ ዕድገት እየደጎመ መሆኑንም አንስተዋል።

የዲጂታል መሰረተ ልማት ከስልክ ጥሪ ያለፈ መሆኑን በመጥቀስ፤ በሁሉም ዘርፍ ውጤታማነትን፣ ጥራትን እና ፍጥነት የመጨመር ራዕዩን እያሳካ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ይህም የግብርናውን ዘርፍ ጨምሮ በንግድ እና በሌሎች ዘርፎች ጭምር መሆኑን አብራርተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...