ኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ሊጀምር ነው

Date:

ኢትዮ ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ ቀደም ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በተጨማሪ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ሊጀምር እንደሆነ አስታውቋል።

የሆስፒታሉ ባለቤት የሆኑት አቶ ብርሀን ተድላ እንደገለፁት ህክምናውን ለመጀመር የሚያስችለውን ቅደመዝግጅት ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ወደስራ ለመግባትም ከጤና ሚንስቴር የሚገኘውን ፈቃድ ብቻ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ውስጥ እንደሚጀመር ከተገለፀው የኩላሊት ንቅለ ተከላ በተጨማሪ ሌሎች አዳዲስ ህክምናዎችን እንደሚጀመሩ ጠቁመዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሆስፒታሉ ወደውጪ ሀገር የሚያስኬዱ ሕክምናዎች በሀገር ውስጥ ለማከናወን የጀመረውን ጥረት ለማጠናከር የሚረዳው የላቦራቶሪ ዲፖርትመንቱ ሁለት የጥራት ዕውቅና ሰርተፊኬት ማግኘቱንም ተናግረዋል።

አቶ ብርሀን ይህንን የገለፁት ሆስፒታሉ የISO 9001/2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፍኬት ማግኘቱን አስመልክቶ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...