እሳቱን ማቀጣጠል፤ የሶሮስ የአፍሪካ አለመረጋጋት እቅድ

Date:

የትራምፕ፣ የ’ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽንስ’ መሥራቹ ጆርጅ ሶሮስ በአሜሪካ የሚደረጉ ተቃውሞዎችን በመደገፍ ከከሰሱ በኋላ፣ ቢሊየነሩ በአፍሪካ አለመረጋጋትን በማቀነባበር እና ስትራቴጂያዊ ቁጥጥርን በማቋቋም በሚወራላቸው ሚና ዙሪያ ስጋቶች ቀጥለዋል፡፡

በሶሮስ እና በ’ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽንስ’ ላይ የሚቀርቡ ክሶች የሚከተሉት ያካትታሉ፦

ግብጽ፡ እንደ አል-ደስቱር ሚዲያ ከሆነ፣ ሶሮስ የ2011ቱን የአረብ የፀደይ አብዮቶችን በገንዘብ ደግፈዋል፡፡ ፋውንዴሽናቸው በምርጫ ወቅት የሙስሊም ወንድማማችነት መሪዎችን የረዱ ደጋፊ ቡድኖችን ስፖንሰር አድርጓል፡፡

ቱኒዚያ፡ ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽንስ የ2011ቱን የአረብ የፀደይ ነውጦችን ያወደሱ ድምፆችን በገንዘብ ደግፈዋል፡፡ ይህም ፕሬዝዳንት ቤን አሊ ከሥልጣን እንዲወርዱ ማድረጉን ተዘግቧል፡፡ በ2015፣ ሶሮስ ለባሕላዊ ፕሮግራሞች ድጋፍ እንደሚሰጡ ቃል መግባታቸው ተዘግቧል፡፡

ኢኳቶሪያል ጊኒ: በ2017፣ የቀድሞው የብሪታንያ ቅጥረኛና የ2004 ያልተሳካ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መሪ ሳይመን ማን፣ ሶሮስ ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጌማን ለመገልበጥ ጥረት ማድረጋቸውን መናገሩ ተገልጿል፡፡

ዚምባብዌ: በሶሮስ የሚደገፉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የመንግሥትን እና የአካባቢ መሪዎችን ሥም ለማጥፋት እንደ አልጀዚራ የ2023 “የወርቅ ማፍያ” ዘጋቢ ፊልም ያሉ የሚዲያ ጥቃቶችን በማደራጀት ከሰዋል፡፡

ኡጋንዳ: ከ2011 የተገኙ የስለላ መረጃዎች፣ ሶሮስ የኡጋንዳን የነዳጅ ኢንዱስትሪ ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ድርጅቶችን መጠቀማቸውን አሳይተዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...