ዘላለም ኩራባቸው  ለአርቲስት መኮንን ላዕከየ1 ሚ. ብር ስጦታ  አበረከተለት

Date:

የአርቲስት መኮንን ላዕከ የ57ኛ ዓመት ልደትን  ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ለፕሮግራሙ አዘጋጆችም እንግዳ የሆነ መረጃ ዝግጅቱ ከመጀመሩ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ፕሮግራሙን ለምትመራው ለአርቲስት ወይንሸት አበጀ  በስልክ ደረሳት::

ይኸውም የዘኩራ ማስታወቂያ ድርጅት ባለቤትና የማስታወቂያ ባለሙያ የሆነው ዘላለም ኩራባቸው ደውሎ፣ በጣም ለሚወደውና ወንድሙ ለሆነው ለአርቲስት መኮንን ላዕከ የልደት ቀን “የፍቅር ሥጦታዬ ነው” ብሎ የአንድ ሚሊዮን ብር ስጦታ እንዳበረከተለት ከታች ካለው መልዕክት ጋር አብሮ ነገራት !!

“የፍቅር ሥጦታ”

” ሠላም አባዬ! አባዬ በጓደኝነት ጎዳና ውስጥ ሦስት ነበርን፤ አንዷን በሞት አጣን (ሰብለ ተፈራ ) እግዚአሔሄር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ ብለን ዝም አልን .. እኛ ግን መንገዱን ቀጠልን፡፡ አባዬ፤ የወንደላጤነት ጓደኛዬ ፣ አባዬ የአባት ጓደኛዬ ፣ አባዬ የጓደኛ ጥላዬ ፣ በኋላም በትዳር ህይወቴ ልጅ ወልጄ አያት አደረኩህ አባዬ ፣ አባዬ የእኔ ፣የእኛ ፣የሁላችን ፣የሁልጊዜ አባዬ የዛሬ ሙሽራዬ እዚህም ደርሰናል:: ብዙ ይቀረናል፤ እንቀጥላለን፤ መኖር ደግሞ ደስ ይላል፤ አይለየን አባዬ !!!”

(ወንድምህ ዘላለም ኩራባቸው)
**
የኪነጥበብ ባለሙያዎችን በማክበርና በመደገፍ ዘወትር ከደግነት ተግባር የማትጠፋውና የመልካም ልብ ባለቤት የሆንከው ውዱ ወንድማችን ዘላለም ኩራባቸው፣ ለአርቲስት መኮንን ላዕከ ስላደረከው የፍቅር ሥጦታ እጅግ አናመሰግናለን:: እግዚአብሔር ይስጥህ :: እንዳንተ አይነት ወንድምን ያብዛልን::

(ይትባረክ ዋለልኝ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...