እስራኤል የኤርትራ መንግስት ደጋፊን አባረረች እርምጃው በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው

Date:

የእስራኤል ባለሥልጣናት የኤርትራ አገዛዝ ደጋፊ እንደሆነ የተለየን አንድ ኤርትራዊ ዜጋ ከሀገሪቱ ማባረራቸው ተዘገበ። የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን እርምጃው በሀገሪቱ የኢሚግሬሽን አፈጻጸም ፖሊሲ በዓይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነ ዘግበዋል።

ይኔት ኒውስ እንደዘገበው፤ ኤርትራዊው ግለሰብ እ.ኤ.አ በ2011 ዓ.ም. በሕገወጥ መንገድ ወደ እስራኤል ገብቶ በሀገሪቱ ይኖር ነበር። ግለሰቡ በፖሊስ ትልቅ ስለት ከእጁ ላይ በማግኘቱ እና ቤተሰቡን በማስፈራራት ወንጀል ተጠርጥሮ በሚያዚያ 2025 በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

በእስር ላይ እያለ፣ ባለሥልጣናት የኤርትራ መንግሥት ደጋፊ መሆኑን መወሰን ችለዋል፤ በዚህም ጉዳዩ ለእስራኤል የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀርቦ፣ ሚኒስቴሩም በእስራኤል የኢሚግሬሽን ሕግ መሠረት ከሀገር እንዲወጣ ፈቃድ ሰጥቷል።

በትናንተናው ዕለት ከጠዋቱ 9፡00 ሰዓት አካባቢ የሕዝብና ኢሚግሬሽን ባለሥልጣን ከውጭ ዜጎች አስተዳደር ጋር በመተባበር የግለሰቡን የማባረር ሂደት አከናውኗል። ይህ እርምጃ በግልጽ የአገዛዝ ደጋፊ እንደሆነ የተለየ ኤርትራዊ ዜጋን እስራኤል ከሀገር ስታስወጣ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ተገልጿል።

ግለሰቡ ከእስራኤል ወደ አዲስ አበባ እና ካምፓላ ከበረረ በኋላ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ከመድረሱ ተዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...