እናት ባንክ በ”አካታች የባንክ አገልግሎት” የተሻለ ሥራ በመስራቱ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀዳሚ ደረጃ መያዙ ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው የኢትዮጵያ ባንኮች የሴቶች አካታች የባንክ አገልግሎት የምዘና መስፈርት መሠረት፣ የመጀመሪያና ብቸኛ ባንክ ሆኖ በመገኘቱ፣ በቀዳሚነት መመዝገቡ ተጠቁሟል፡፡
ብሔራዊ ባንክ የባንኮች ሁሉን አካታች የባንክ አገልግሎቶች በተመለከተ ካስቀመጣቸው መስፈርቶች መካከል፣በተለይ ለሴቶች የተለየ የባንክ አገልግሎት በማቅረብና በፈጠራ የተደገፈ የባንክ አሠራር በመዘርጋት ቀልጣፋ የሆነ አገልግሎት መስጠት ተጠቃሽ ናቸው ተብሏል፡፡
በዚህም መሰረት እናት ባንክ፣ ሴቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርግ አካታች የባንክ አገልግሎት አሰራር ዘርግቶ በመስራቱና ሌሎች ሴቶችን በንግዱ ዘርፍ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን በማከናወኑ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተቀመጠው መለኪያ ቀዳሚ ደረጃ ላይ መመዝገቡን እናት ባንክ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
