ኪም ጆንግ ኡን ይህን ያሉት የሀገሪቱ አየር ኃይል በአየር ጥቃት መፈፀምና እና የአየር ጥቃትን መከላከል ዙሪያ ያካሄደውን ወታደራዊ ልምምድን በአካል በመገኘት በታደሙበት ወቅት ነው ተብሏል።
የሰሜን ኮሪያ አየር ኃይል ያካሄደው ወታደራዊ ልምምድ ከመካከለኛ እስከ ረጅም ርቀት መጓዝ የሚችል ሩስያ ሰራሽ ሚሳኤል የማስወንጨፍ ሙከራን ያካተተ ስለመሆኑ መረጃው ጠቁሟል።
“ሁሉም የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ኃይል የላቀ የጦር ዝግጅት ማድረግ አለበት” ብለዋል የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ወታደራዊ ልምምዱን በተመለከቱበት ወቅት።
ሰሜን ኮሪያ ዓለም አቀፍ የፀረ ሽብርተኝነት ዘመቻን በሙሉ ልብ እየደፈገች አይደለም በሚል በአሜሪካ ከሚጠቀሱ ሀገራት ውስጥ መካተቷን እንደማትቀበለውም አስታውቃለች።
አሜሪካ እ.አ.አ. ከ1997 ጀምሮ የፀረ ሽብር ዘመቻዎችን ከማይደግፉ ሀገራት መከከል ሰሜን ኮሪያን ያላካተተችበት ወቅት አለመኖሩን የጠቀሰው የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ለሚቃጣባት ማንኛውም ጥቃት ተገቢውን ምላሽ እንደምትሰጥ ገልጿል።
