እንግሊዝ በግብፅ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ላልተወሰነ ጊዜ  ዘጋች

Date:

እንግሊዝ በግብፅ የሚገኘውን ኤምባሲዋን መዝጋቷ የተገለጸ ሲሆን፤ ኤምባሲው የተዘጋው የግብፅ መንግሥት በካይሮ ለሚገኘው ኤምባሲ የሚሰጠውን ጥበቃ በማቆሙ ነው ተብሏል።

ይህን ተከትሎ የእንግሊዝ መንግሥት ኤምባሲው ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ አስታውቋል።

የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ የጀመረው ግብፃዊ አክቲቪስት በለንደን ከሚገኘው የግብፅ ኤምባሲ አጠገብ ተይዞ መታሰሩን ተከትሎ  ነው ተብሏል።

አክቲቪስቱ በአሁኑ ወቅት ከእስር መለቀቁ ቢገለጽም፣ የሀገራቱ ውጥረት ተባብሶ ቀጥሏል።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ፣ የእንግሊዝ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጆናታል ፖወልን ስለእስሩ ማብራሪያ መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፤  በግብፅ የሚገኙ ዜጎቿ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
‎
‌‎የግድቡ ባለቤት የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ ለግድቡ ግንባታ ሂደት አስተዋጽኦ ላበረከቱት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...