ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ንጉሡ መልኳ ውብ የሆነች ብላቴና ሊያገባ ወዶ መልእክተኞችን መርጠው ያመጡለት ዘንድ ላከ

Date:

እነርሱም መላ ሀገሪቱን ሲያስሱ ቆይተው ሮሜ ውስጥ ባለ አንድ ገዳም ውስጥ ከሌሎች ደናግል ጋር ያገኟትን ቅድስት አርሴማ ሲያገኙ ሥዕሏን ስለው ለንጉሡ ላኩለት። እናታችን ራሷን የክርስቶስ ሙሽራ አድርጋ የለየች የፊቷ መልክ እጅግ ልዩ፣ ደምግባቷ ያማረ ነበረች። ንጉሡም ይህን ሥዕል እንዳየ እጅግ ወደዳትና እንዲያመጡለትም አዘዘ።

ደናግልኑ ይህን እንደሰሙ ከቅድስት አርሴማና ከገዳሙ እመምኔት ቅድስት አጋታ ጋር ሸሽተው ወደ አርማንያ ሄዱ። አካባቢው ንጉሥ ድርጣድስ የሚገዛው ነበርና ከንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ መልእክት ደርሶት ሲያስፈልጋት ከደናግሉ ጋራ አገኛቸው። እርሱም በውበቷ በእጅጉ ተስቦ ይህችን ውብ ሴትማ ለራስ ነው እንጂ ለሌላ አሳልፎ መስጠት አይገባም ለራሱ ፈልጎ እዚያው አኖራት።

ከደናግሉም ጋራ ካሠራቸው በኋላ እናታችን ቅድስት አርሴማን በብዙ ሊያታልላት ሞከረ። እርሷ ግን በመንፈሳዊ ሕይወቷ ፍጹም ራሷን አሳልፋ የሰጠች፣ ራሷንም ለቸሩ አምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ ያደረገች ናትና ለሰማያዊ ሙሽርነቷ የታመነች ሆነች።

ንጉሡም ደጋግሞ ቢሞክር አልሆንለት አለ። በኋላም እመ ምኔቷን እንድታባብላት ላካት፤ እመ ምኔቷ ግን “አይዞሽ! እንዲህ ላለው ምድራዊ ኃላፊ ነገር እንዳትታለይ፤ ሰማያዊ ሙሽርነትሽንና ንጽሕናሽን አጽኚ” ብላ ይበልጥ አጸናቻት። ንጉሡም በግድ ይዟት ሊሄድ ቢል ኃይለ መንፈስ ቅዱስ አድሮባት ነበርና ያንን በጦር የጎለመሰ ሰውነት ያለውን ብርቱ ጦረኛ ከመሬት ፈጠፈጠችው።

ንጉሡም አንዲት ትንሽ ወጣት እንደምን ጣለችኝ ብሎ እጅግ አፈረ። እጅግም ተቆጥቶ ቅድስት አርሴማን ሥቃይዋን ሊያበዛባት ተነሳ እርሷንም በደናግሉ ሁሉ ፊት አሠራትና በፊቷ አንድ በአንድ አንገታቸውን ቀላቸው።

እርሷ ግን “አይዟችሁ!” እያለች ታጽናናቸው ነበር። ይልቁንም ትሳቀቃለች ብሎ ባደረገው ነገር ቅዱሳኑ ሰማያዊ አክሊልን ሲቀበሉ ትመለከት ነበር። ይህን ሲጨርስም “አንቺን እንደሌሎቹ ቶሎ አልገድልሽም” ብሎ በብዙ መከራ እጅግ አሠቃያት።

በመጀመሪያ ሁለቱን ጡቶቿን ቆረጠ፤ ቀጥሎም ሁለቱን ዐይኖቿን አወጣቸው፤ እርሷም እንዲህ ሳለች ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ የብርሃን ዐይኖችን ሰጠቻት።

በመጨረሻም እርሷን ማሠቃየት ሲሰለች ከቀሩት ከሰባ አምስት ወንዶችና ከሃያ ሰባት ደናግል ሴቶች ጋራ መስከረም ሃያ ዘጠኝ ቀን አንገቷን ሰየፋቸውና የሰማዕትነትን የድል አክሊል ተቀዳጁ። ታኅሣስ 6 ቀንም የቅድስቲቱ ሰማዕት ቤተክርስትያኗ የከበረችበትና አብረዋት ከተጋደሉ 27 ደናግላን ጋር ሥጋቸው የፈለሰበት ነው።

ቅድስት አርሴማ ከሃያ ሰባቱ ደናግል ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበለች በኋላ ንጉሡ ድርጣድስ ፈጽሞ ታመመ ታወከም። በትውፊት ታላቅ ወንድሟ እንደኾነ የሚነገርለት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳሳትን አስቀድሞ አሥሮት ነበር።

በኋላም ቅዱስ ጎርጎርዮስን ፈታውና ከደዌው ዳነ፤ የቅዱሳን ደናግልና የቅድስት አርሴማንም የቅዱሳን ሰማዕታቱን ዐፅመ ፍልሠታቸው ታኅሣሥ ስድስት ቀን በቅዱስ ጎርጎርዮስ ተደረገ፡፡ እንዲሁ ደግሞ የእርሷ ማኅበርተኞች የሚባሉ የመቶ ዐሥራ ዘጠኝ ሰማዕታት ዝክራቸው ነው።

በስሟ ያማረ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው አከበሩበት። ቅድስት አርሴማ በሰማዕትነት ስታርፍ ጌታችን ነፍሷን በክብር ተቀበላት ራሷን ለእርሱ በሙሽርነት አሳልፋ ሰጥታለችና ብዙ ቃል ኪዳንም ሰጣት፡፡

በቃል ኪዳኗ የታመኑ ገዳማውያን ዘወትር አማልጂን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንሳተፋለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...