ከማደርጋቸው የንግድ ድርድሮች ሁሉ ከባድ የሆነብኝ ድርድር የጠረፍ ንግድ ድርድር ነው ሲል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናግሯል

Date:


የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከአለም ንግድ ድርጅት፣ የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (COMESA) በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ላይ እንደራደራለን ከባድ የሆነብን ድርድር ግን የጠረፍ ንግድ ድርድር ነው ብለዋል፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ከኋላው የሚገፋው አካል ስላለ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል የሞያሌ ከተማ ንግድ ምክር ቤት ከኬንያ ጋር ለመተግበር በተፈጸመው ውል ላይ የቀረበውን ቅሬታ ሚኒስቴሩ እንደማይቀበለው ተናግረዋል፡፡

የሞያሌ የንግድ ምክር ቤት የስምምነቱ ነፃ የንግድ ቀጠና ስፋቱ፣ በኬንያ በኩል 100 ኪሎ ሜትር  መሆኑን መናገሩ ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል ግን 50 ኪሎ ሜትር ብቻ መሆኑ ተገቢ እንዳልሆነ የተናገረው ምክር ቤቱ ምክንያቱም አርብቶ አደር የሆነው የአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚ አይሆንም ፤ በ50 ኪ.ሜ. ርቀት ውስጥ ያሉት ከተሞችም ጥቂት ስለሆኑ፣ ቢያንስ ከድንበር እስከ 300 ኪ.ሜ ይሁንልን የሚል ጥያቄ ምክር ቤቱ መጠየቁን የተናገሩት ሚኒስትሩ ይህ የማይሆን ነው ብለዋል፡፡

ያን ያህል ርቀት ክፍት አደረግን ማለት በወጪ ንግድ ላይ ከፍተኛ ጫና ያሣድራል ማለት ነው  ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...