የኢራኑ ፕሬዚዳንት በአደባባይ

Date:

የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን የአሜሪካን እና እስራኤልን ጥቃት ለማውገዝ ከህዝባቸው ጋር ለተቃውሞ ወደ አደባባይ ወጡ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ድርጊቱን ለማውገዝ በተጠራው ሰልፍ ላይ በዋና ከተማዋ ቴህራን ታይተዋል።

አሜሪካ በኢራን የኑክሌር ማብላያ ጣቢዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ ነው ሰልፎች እየተደረጉ ያሉት፡፡

“ሞት ለአሜሪካ !” በሚል መፈክር ዜጎች አደባባይ በወጡበት አጋጣሚ ፕሬዚዳንቱ አብረው መታየታቸው የጉዳዩን አሳሳቢነት ይጠቁማል ተብሏል።

በጸረ-አሜሪካው ተቃውሞ ላይ ከተማሪዎች ጋር ሲንቀሳቀሱ ታይተዋል ማሱድ ፔዜሽኪያን፡፡

“ለትልቁ ጦርነት ተዘጋጅተናል” የሚሉ ጽሁፎችም በቴህራኑ ተቃውሞ ላይ ጎላ ብለው ሲታዩ እንደነበር መህር ኒውስ አስነብቧል፡፡

ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን የአሜሪካን ጥቃት ያወገዙ ሲሆን፣ ጥቃቱ የዓለምን ህግ እና ሥርዓት እንደመናድ ይቆጠራል በሚል ቀደም ሲል መኮነናቸው አይዘነጋም፡፡

በሄግ ኒዘርላንድስ ፣ በለንደን እንግሊዝ እና በኒው ዮርክ  አሜሪካ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...