ከሳዑዲ ዓረቢያ ከ2 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

Date:

በሳዑዲ ዓረቢያ በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 86 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከተመላሾቹ መካከል 1 ሺህ 664 ወንዶች፣ 387 ሴቶች እና 35 ሕፃናት ይገኙበታል። ከጠቅላላው ተመላሽ ዜጎች መካከል 63ቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸውም ተገልጿል።

ዜጎቹ ወደ ሀገር ቤት ከደረሱ በኋላ በአውሮፕላን ማረፊያውና በማቆያ ማዕከላት አስፈላጊው ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው ሲሆን፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማቀላቀል ሥራም እየተከናወነ መሆኑ ተጠቁሟል።

በመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የተጀመረው ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ መርሐ ግብር ቀጥሎ እየተከናወነ ሲሆን፣ እስካሁን ከ116 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የተመላሽ ዜጎችን መቀበል ከጉዞ ሂደት በተጨማሪ ሰብዓዊ ድጋፍን፣ የመብት ጥበቃንና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራን የሚጠይቅ ሂደት ነው። በተለይም ሴቶች፣ ሕፃናትና ታዳጊዎች ተገቢውን እንክብካቤና ድጋፍ ማግኘታቸው አስፈላጊ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጋዜጠኛ ቤተልሔም ተስፋዬ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ

በ39 ዓመቷ በትላንትናው ዕለት በድንገት ሕይወቷ ያለፈው ታዋቂዋ ጋዜጠኛ...

የገዛ ልጁን በአንካሴ ወግቶ ገደለ

በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረ ጊዜያዊ አለመግባባት ምክንያት የገዛ ልጁን...

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሆንግ ኮንግና በኔዘርላንድስ አሸነፉ

በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲነም ደረጃ በተሰጠው የሆንግ ኮንግ ግማሽ ማራቶን...

የመንግሥት ሠራተኞች የሙያና የሥራ ባህሪ በተቀናጀ የምዘና ሥርዓት ሊመዘን ነው

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን (FCSC) የመንግሥት ሠራተኞችን ሁለንተናዊ ብቃት...