በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲነም ደረጃ በተሰጠው የሆንግ ኮንግ ግማሽ ማራቶን ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ድል አስመዝግበዋል።
የ2026 ባንክ ኦፍ ቻይና ሆንግ ኮንግ-ዙሃይ-ማካዎ ግማሽ ማራቶን በወንዶቹ አትሌት አዲሱ ጎበና በ1:01:35 አሸንፏል ።
አትሌት አሊዪ ቃሲም በ1:02:31 በመግባት ሁለተኛ ወጥተዋል ።
አትሌት ታፈረ አዲሱ በ1:05:37 8ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
በሴቶች ምድብ አትሌት ውዴ ከፋሌ በ1:09:04 በመግባት አሸንፋለች ።
አትሌት ፋንቱ ወርቁ በ1:09:16 ሦስተኛ ፣አትሌት ባራኪ ረዳኢ በ1:09:53 አራተኛ ፣አትሌት አስማረች አንለይ 1:10:23 አምስተኛ እና አትሌት ዘውዴ ውዱ በ1:12:10 9ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በኔዘርላንድስ በተካሄደ በ15 ኪ.ሜ አትሌት አሳየች አይቸው የዓለም 2ኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ በድንቅ ብቃት አሸንፋለች።
አትሌት አሳየች ውድድር 45:29 በመግባት ነው ማሸነፍ የቻለችው።
