ከአስቃቂው የአውሮፕላን አደጋ የተረፈችው ሕንዳዊት…

Date:

ቡሚ ቹሃን በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ከበረራ ሰዓት በ10 ደቂቃ ዘግይታ በመድረሷ ከአሰቃቂው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ መትረፍ ችላለች፡፡

ቡሚ ቹሃን የቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ተማሪ ስትሆን ከባለቤቷ ጋር በእንግሊዝ ብሪስቶል ኑሮዋን አድርጋለች፡፡

በቅርቡም የእረፍት ጊዜዋን ከቤተሰቦቿ ጋር ለማሳለፍ ወደ ምዕራብ ሕንድ አቅንታ ነበር፡፡

የእረፍት ጊዜዋ ሲጠናቀቅም ወደ ለንደን ለመመለስ በበረራ ቁጥር 171 አውሮፕላን ትኬት መቁረጧን ትናገራለች፡፡

የበረራ ሰዓቱ ሲደርስም ቦሆሚ ቻውሃን ወደ አህመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ ማቅናት ትጀምራለች፡፡

ይሁን እንጂ ወደ አውሮፕላን ማረፊያው እየሄደች ባለችበት ወቅት ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ያጋጥማታል፡፡

አሕመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያም ከበረራ ሰዓት በ10 ደቂቃ ዘግይታ ትደርሳለች፤የሚመለከታቸው አካላትም ወደ ውስጥ እንዳትገባ ከለከሏት፡፡ይህን ተከትሎም በረራው አመለጣት፡፡

ትረፊ ያላት ነፍስ እንዲሉ… በረራ ያመለጣት ቡሚ ቹሃን ከንዴቷ ሳትወጣ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ወደለንደን ልትጓዝበት የነበረው አውሮፕላን መከስከሱን በሥፍራው ተገኝታ አይታለች፡፡

ቡሚ ቹሃን የትራፊክ መጨናነቅ ሕይወቴን ታደገው ስትል መናገሯንም ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡

(ኤፍ ኤም ሲ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...