ኢራን 150 ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ተኮሰች

Date:

የአሜሪካ ጦር ወደ እስራኤል የተተኮሱትን የኢራን ሚሳኤሎችን ለመምታት መርዳቱን ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ትናንት በተጀመረውና የኢራንን የተለያዩ ቦታዎች ካጠቃው የእስራኤል ወታደራዊ እርምጃ ተከትሎ ኢራን ማምሻውን በእስራኤል ከተሞች ላይ የሚሳኤል ጥቃት ፈፅማለች፡፡

ኢራን በፈፀመችው ጥቃት እስካሁን 150 የሚሆኑ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል መተኮሷ ተገልጿል፡፡

በተለያዩ የቴል አቪቭ ቦታዎች ላይ በወደቁት የኢራን ሚሳኤሎች ምክንያት የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሰራተኞች መሰማራታቸውም ተነግሯል።

በዚህ የኢራን የሚሳኤሎች ጥቃት እስካሁን 40 እስራኤላውያን መጎዳታቸውንና ሁለቱ የከፋ ጉዳት እንዳጋጠማቸው ቲአርቲ ዘግቧል።

የኢራንን ሚሳኤሎች ለማክሸፍ እስራኤል አይረን ዶም ፀረ ሚሳኤሎችን መተኮሷም ነው የተገለፀው፡፡

ከዚህ ጥቃት በኋላ መግለጫ የሰጡት የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ፤ ኢራን አሁን ቀይ መስመር አልፋለች፤ ለዚህም የኢራን መንግስት ዋጋ ይከፍላል ብለዋል።

በጥቃቱ ላይ የአሜሪካ ጦር ወደ እስራኤል የተተኮሱትን የኢራን ሚሳኤሎችን ለመምታት እርዳታ መስጡትን ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናት መግለጻቸውን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...