ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ሽልማት ለዳካር የወጣቶች ኦሎምፒክ ጀግኖች ተበረከተ

Date:

በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የ2026 የዓለም ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ በስኬት ላስጠሩ ወጣት አትሌቶችና አሰልጣኞች ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ሽልማትና ዕውቅና ተበርክቷል።

በአፍሪካ አህጉር ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር፣ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ 5 የወርቅና 3 የብር ሜዳሊያዎችን በድምሩ 8 ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ የአትሌቲክስ ሜዳሊያ ሰንጠረዡን በቀዳሚነት መጨረሷ ተገልጿል።

ለውጤቱ ያበቁ ወጣት አትሌቶችና አሰልጣኞች የዕውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው ብሉ ናይል አቫንቲ ሆቴል ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዶ/ር አክሊሉ ታደሰ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣ አሰልጣኞች፣ አትሌቶችና የሚዲያ ተወካዮች ተገኝተዋል።

በቀረበው የሽልማት መረጃ መሠረት፣ የወርቅ ሜዳሊያ ላስመዘገቡ አትሌቶች ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር 1.5 ሚሊዮን ብር፣ ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ 1 ሚሊዮን ብር በድምሩ 2.5 ሚሊዮን ብር ለእያንዳንዳቸው ተመድቧል።

የብር ሜዳሊያ ላስመዘገቡ አትሌቶች ከሚኒስቴሩ 750 ሺህ ብር፣ ከኦሎምፒክ ኮሚቴው 500 ሺህ ብር በድምሩ 1.25 ሚሊዮን ብር ለእያንዳንዳቸው ተበርክቷል።

የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዎቹ ጁነዲን አብዶ፣ ወቢ ወጅራ፣ ዮሚፍ አበበ፣ ኤልሳቤጥ አማረና ነፃነት ሰለሞን ሲሆኑ፣ የብር ሜዳሊያ አሸናፊዎቹ ዮርዳኖስ ጽጋብ፣ ጎይቶም መኮንንና ጻድቃን መኮንን ናቸው።

ወጣት አትሌቶቹን ለዚህ ውጤት በማብቃት የተጫወቱትን ሚና በማድነቅ ለአሰልጣኞችም የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል።

አሰልጣኝ ንጹህ ወንድሜነህ፣ አሰልጣኝ ቴዎድሮስ ኃይሉና ኮማንደር ቶሌራ ዲንቃ በሽልማት ዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ሲሆን፣ ለሕክምና ባለሙያዋ ዶ/ር ቃልኪዳንም ሽልማት መበርከቱ ተጠቅሷል።

በዳካር የተመዘገበው ውጤት ለኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ወደፊት ተስፋ የሚሰጥ ስኬት ሲሆን፣ ለወጣት ስፖርተኞች የተሰጠው ዕውቅናና ሽልማትም የስፖርት ስኬትን ለማበረታታት የተወሰደ እርምጃ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አትሌት ሱሌ ኡቱራ የፍትህ ጥሪ አቀረበች

አትሌት ሱሌ ኡቱራ ያለኝን ሀብት በፍርድ ተዛብቶ ተቀማሁ በማለት...

ከድሬዳዋ እስከ ዱባይ የተዘረጋው የሌብነት ሰንሰለት፤ ተከሳሾቹ እስከ 14 ዓመት ከ4 ወር እስራት ተቀጡ

በድሬዳዋ ከተማ ከመኖሪያ ቤት የተለያዩ ዘመናዊ ሞባይል ስልኮችን በመስረቅ...

ኢትዮጵያ ወረርሽኞችን ቀድሞ የመከላከልና ፈጥኖ የመቆጣጠር አቅሟን እያጎለበተች ነው

ኢትዮጵያ ሀገራዊ አቅሞችንና ዓለም አቀፍ ትብብሮችን በማቀናጀት ወረርሽኞችን ቀድሞ...

አረንጓዴ አሻራ በተመድ ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘ

ኢትዮጵያ ለኮፕ 32 አዘጋጅነት እንድትመረጥ አስተዋጽኦ ያደረጉት የአረንጓዴ አሻራ...