ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ በዓለ ኪዳነ ምህረት ነው

Date:

እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችም፡፡


እመቤታችንም “ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መጥተህ ልምናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም እናቴ ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡

እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን፣ ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን፣ በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጻውን፣ መባዕ የሰጠውን፣ ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን፣ ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡ ጌታችንም የካቲት 16 ቀን ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ በራሴ በባሕርይ አባቴ በአብና ማሕየዊ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ ቃል ኪዳን ገባሁልሽ ብሏት አርጓል፡፡

ዕለቱም በየዓመቱ በዓለ ኪዳነ ምህረት ተብሎ ይከበራል፡፡ ዳግመኛም በዚህ ዕለት 78 ነፍሳት የበላውን ስምኦን በላኤ ሰብዕ አማልዳ አድናዋለች፡፡ ስምኦን እንደ አብርሃም እንግዳ መቀበል የሚወድ ነበር፡፡ ዲያብሎስም እንግዳ መስሎ መጥቶ እንደ አብርሃም ልጅህን አርደህ አብላኝ ብሎት ሲያርድለት ቅመስልኝ አለው፤ ሲቀምስም በዚያው ሰው መብላትን አሳድሮበት ሔደ፡፡

ከዚያ በኋላም ከቤተሰቦቹ፣ ከልጆቹና ከጎረቤቶቹ ጀምሮ 78 ነፍሳትን በልቷል፡፡ ከዚያ በኋላም አንድ በቁስል የተመታ ሰው ተመልክቶ ሊበላው ቢፈልግም ተጸየፈው፡፡ ሰውየው ግን ውሃ አጠጣኝ አለው፤ አልፎት ሊሔድ ሲል በሥላሴና በቅዱሳን መላዕክት ስም ለመነው፡፡

ዝም ብሎት ሲሔድ በእመቤታችን ስም ቢለምነው ከያዘው ውሃ አጠጣው፡፡ በሞቱ ጊዜም በስሟ መጽውቷልና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቃል ኪዳኗ ከሲኦል እሳት አድናዋለች፡፡ በዚህ ቃል ኪዳኗ የታመኑ ገዳማውያን ዘወትር ቅድስት ሆይ ለምኝልን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391 ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...