ዓባይ ባንክ ያልተጣራ 4.3 ቢሊዮን ብር አተረፈ

Date:

ባንኩ ይህንን ያለው 15ተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ባለበት ወቅት ሲሆን በበጀት አመቱ ያገኘው ገቢ ከ2016 በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር የ120 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል።

በተጠናቀቀው በጀት አመት ባንኩ የተቀማጭ ገንዝብ መጠኑን ከባለፈው ዓመት በ37 በመቶ በማሳደግ 72 ቢሊዮን ብር ያደረሰ ሲሆን ጠቅላላ ሀብቱም የ38 በመቶ እድገት በማስመዝገብ 93 ቢሊዮን ብር ሆኗል ።በ2017 በጀት ዓመት ዓባይ ባንክ ያልተጣራ 4.3 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታዉቋል፡፡

ባንኩ ለተለያየ የኢኮኖሚ ዘርፍ የሰጠው ጠቅላላ የብድር መጠንም 47.5 ቢሊዮን ብር መድረሱን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ የኋላ ገሠሠ ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢውን የ95 በመቶ እድገት በማሳየት 16.2 ቢሊዮን ማድረሱን ተናግረዋል።

ከ555 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ባንኩ  የዲጂታል ባንከ አገልግሎት አማራጮችን በማቅረብ የደንበኞቹ ን ቁጥር ከ4 ሚሊዮን በላይ ማድረሱን ተናግሯል።

አባይ ባንክ በ823 መሰራች ባለአክሲዮኖች 125.8 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ሥራ የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የባለአክሲዮኖችን ቁጥሩ 4,500 በማድረስ የተከፈለ ካፒታሉን 7 ቢሊዮን ብር ማድረሱን ገልጷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...