31ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፈዴሬሽን መደበኛ ኮንግረስ ትናንት ማምሻውን ተጠናቅቀዋል ።
በናጄነሪያዋ፣ ኡጉኑ ስቴት አቡኩታ ከተማ የተካሄደው 31ኛው መደበኛ ኮንግረስ በዓለም አትሌቲክስ ፕሬዝዳንት ሎርድ ሰባስቲያን ኮ የቪድዮ መልዕክት የተከፈተ ሲሆን ጉባኤ የ2024 የኮንፈደሬሽኑ የክንውን ሪፖርት ቀርቧል።
የአፈፃፀም ሪፖርቱም በኤክስኪውቲቭ ቺፍ ኦፊሰሩ ሚስተር ላሚን ፋቲ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በተጨማሪም የአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና አስተናጋጇ ሃገር ናይጄሪያ አጭር ጊዜም ቢሆን ለሻምፒዮናው ስላደረጉት ዝግጅት ዝርዝር መረጃ አቅርቧል ።
እንዲሁም የ2026 የአፍሪካ ሲኒየር አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዘጋጅ ሃገር ጋና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሚስተር ባዋ የሻምፒዮናው እቅድ አቅርበዋል።
ከጉባኤው ተሳታፊዎች “ኢትዮጵያ በእድሜ ተገቢነት” ላይ እየወሰደች ያለችውን ስራና ቁርጠኝነት እንዲሁም እርምጃ አድናቆት የተሰጠው ሲሆን ለሌሎች ሃገራት ተሞክሮ እንደሚሆን ተገልጿል።
በጉባኤው ኢትዮጵያን ከወከሉ የፌዴሬሽኑ አመራሮች በተጨማሪ ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን እና የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት በካውንስልና በኮንግረስ ስብሰባዎች ላይ ተካፍለዋል።
በኮንግረሱ የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ።
በመጨረሻም የጉባኤውን ባለ አስራ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣትና በኮንፈዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ሚስተር ሃማድ ካልካባ ማልቡም የመዝጊያ መልዕክት ኮንግረሱ ተጠናቋል።
