ዘመን ባንክ “የኢኮኖሚ ሊበራላይዜሽንና የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ የወደፊት አቅጣጫ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ልዩ የፓናል ውይይት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት አካሂዷል ፡፡
በውይይቱ ላይ የባንኩ ባለአክሲዮኖች፣ ኮርፖሬት ደንበኞች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የፋይናንስ ባለሙያዎች፣ ምሁራንና መገናኛ ብዙኃን ተሳትፈዉበታል፡፡
በሙያው ከፍተኛ እውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያም መነሻ ሃሳብ አቅርበው በተሳታፊዎች የሃሳብ ልውውጥ ተደርጓል ፡፡
ይህ ወቅታዊ ውይይት የተዘጋጀው ሀገራችን በኢኮኖሚና በፋይናንስ ዘርፎች ላይ ቁልፍ የሆኑ ሪፎርሞችን እያካሄደች ባለችበት ወቅት መሆኑ የኢኮኖሚ ሊበራላይዜሽንና የባንክ ዘርፍ የወደፊት አቅጣጫ በመቅረጽ ረገድ ለፖሊሲ አውጪዎች የባለሙያና የባለድርሻ አካላትን አስተያየት ለማግኘት እንዲረዳ ታስቦ ነዉ ተብሏል፡፡
ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም
