“ዛሬም ድረስ የሰው ልጅ በወባ በሽታ ሲሞት ማየት ያሳፍራል”

Date:

ከተመሰረተ 27 አመታት ያስቆጠረው የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር፣ ዛሬም ድረስ የሰው ልጅ በወባ በሽታ ሲሞት ማየት ያሳፍራል ብሏል።

እንደ ሀገር እንደማህበርና እንደ ግለሰብ፣ የወባ በሽታን በመከላከል ረገድ ሰፊ ስራ የተሰራ ቢሆንም፣ ዛሬም ድረስ የሰው ልጅ በዚሁ በሽታ ህይወቱ እያለፈ መሆኑ መስማት ያሳዝናል ሲል ገልጿል።

ማህበሩ ይህንን ያለው የተመሰረተበትን 27ኛ አመቱን ለማክበር በተሰናዳበት ወቅት ነው።

በሀገራችን   በ1990 ዓ.ም የተከሰተውን የወባ ወረርሽኝ ተከትሎ የተመሰረተው ማህበሩ፤ ዛሬ ላይ በ10 ክልሎች የመከላከል ስራውን እየሰራ ይገኛል።

የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር ከ27 አመት በፊት የጎጃም አካባቢን ትኩረት አድርጎ የጀመረውን እንቅስቃሴ በተሞክሮዎቹ በማጎልበት አድማሱን በማስፋት አሁን ላይ ሶስት ድርጅቶች አቅፏል።

የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር መስራች የሆኑት እና ለ27 አመታት ማህበሩን ከምስረታው አንስቶ የመሩት አቶ አበረ ምህረቴ እንደተናገሩት፤ ማህበሩ 27ኛ አመቱን ሲያከብር ሁለት አላማዎችን አንግቦ እንደሆነ ገልጸዋል።

ከነዚህም መካከል የማህበሩ የ27 አመት ጉዞው ለታሪክ እንዲቆይ፣ ሌሎችም ድርጅቶች ታሪካቸውን ጽፈው እንዲያስቀምጡ ቀስቃሽ ለማድረግ ነው ብለዋል። ሁለተኛው አላማ ደግሞ “ፈጥኖ ደራሹ ማኀበር” የተሰኘ መጽሐፍ የተዘጋጀ ሲሆን መጽሐፉም  ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ይመረቃል ብለዋል።

እንደዚሁም በወባ ላይ የሚደረገውን  ርብርብ ለማነሳሳትና ህብረተሰቡ እንዳይዘናጋ ማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሁሉም ሰው በዓመት 1ሺህ 200 ብር ለፀረ ወባ ማህበር በማዋጣት አባል በመሆን ተረባርበን ወባን ማጥፋት አለብን ሲሉም አቶ አበረ ምህረቱ  ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...