የህወሀትና ፌደራል መንግሥት ውዝግብ

Date:

የኢትዮጵያ መንግሥት የፈረመውን ውል ከማክበር በተቃራኒ ትግራይን የሁከት ማእከል ለማድረግ እና የትግራይ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዳያገግም የሚያደርጉ ክልከላዎች አጠናክሮ በመቀጠል ተጠምዷል ሲል ህወሓት ከሰሰ።

ህወሓት የፕሪቶርያ ስምምነት እንዲፈፀም በተደጋጋሚ ጥሪ እያቀረበ እንዳለ በመግለፅ የሚጀምረው የህወሓት መግለጫ፥ ይሁንና የኢትዮጵያ መንግሥት የፈረመውን ውል ከማክበር በተቃራኒ ትግራይን የሁከት ማእከል ለማድረግ እና የትግራይ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዳያገግም የሚያደርጉ ክልከላዎች አጠናክሮ መቀጠል መርጧል በማለት ይከሳል።

በፕሪቶርያ ውል መሠረት ታጣቂዎችን ከትግራይ መሬት ማስወጣት የሚጠበቅበት የኢትዮጵያ መንግሥት ይህ ወደጎን በማለት ታጣቂዎቹን በማጠናከር ላይ ይገኛል ሲልም ህወሓት በሳምንታዊ መግለጫው ጨምሮ ገልጿል።

አያይዞም መቋጫ ያላገኘውን የተፈናቃዮች ጉዳይ ያነሳው ህወሓት፥ ታጣቂዎች አሁንም ተቆጣጥረዋቸው ካሉ አካባቢዎች በየጊዜው ዜጎች እየተፈናቀሉ ነው፥ በየወሩ በአማካኝ ከ250 እስከ 300 የሚደርሱ ዜጎች ተፈናቅለው በሸራሮ በኩል መጥተው ወደ የተፈናቃዮች መጠልያ እንደሚገቡ አመልክቷል።

በፌደራል መንግሥቱ ላይ በርካታ ክሶችን ያነሳው የህወሓት መግለጫ፥ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ የተረጋጋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ለሸቀጦች መንገድ መዝጋት፣ ነዳጅ መከልከል፣ የኢንቨስትመንት ሥራዎች እንዲቋረጡ ማድረግ እና ሌሎች ነጥቦች አንስቷል። 

ጉዳዩን አስመልክተው ለህወሓት ልሳን ወይን የተናገሩት የህወሓት ሥራ አስፈፃሚኮሚቴ አባል አቶ ተኽላይ ገብረመድህን ከፕሪቶርያ ውል አፈፃፀም ጋር በተገናኘ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት፣ ለማስተካከል ከፌደራል መንግሥቱ ጋር መነጋገር እንደሚያስፈልግ በማንሳት፥ የአፍሪካ ሕብረት ፖነል ሊጠራ ይገባል ብለዋል።

አቶ ተኽላይ «የአፍሪካ ሕብረት ፓነል ቆሞ ነው ያለው። ይህ ስህተት ነው። አሁንም ቢሆን በአስቸኳይ ዳግም ሊቀጥል፣ ውይይት ሊደረግ ይገባል። የፕሪቶርያ ውል አብዛኛው ያላለቀ እና ጨርሶ ያልተሠራ በመሆኑ፥ ይህ ሊፈፀም ከሆነ መነጋገር መቻል አለብን» ብለዋል።

ከፕሪቶርያ የተኩስ ማቆም ስምምነት አፈፃፀም እንዲሁም ከተፈናቃየች ወደ ቀዬአቸው መመለስ ጋር በተገናኘ ህወሓት እና የኢትዮጵያ መንግሥት ከሚያወዛግቡ አጀንዳዎች መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው። በእነዚህ ጉዳዮች አንዱ ሌላውን ይከሳል።

በዚህ መካከል በትግራይ የተፈናቃዮች ሁኔታ ከመጥፎ ወደከፋ ተሸጋግሯል። ግጭት እንዳይፈጠር በሕዝቡ ዘንድ ስጋት ተፈጥሯል፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታው ተመሰቃቅሏል። 

እነዚህ ህወሓት በሚያነሳቸው ክሶች እና ሌሎች ጉዳዮች ከኢትዮጵያ መንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...