የሆሊውድ “ዎክ ኦፍ ፌም” ኮከብ ያገኘች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ዘፋኝ 

Date:

ቤኒናዊቷ አንጀሊክ ኪጆ በሆሊውድ የንግድ ምክር ቤት ተመረጠው በሎስ አንጀለስ ዝነኛው “ዎክ ኦፍ ፌም” ኮከብ ከሚቀበሉ 36 አርቲስቶች አንዷ ሆናለች።

🌟 ከሉፒታ ኒዮንግኦ፣ ቻርሊዝ ቴሮን እና ባሲል ራትቦን ከመሳሰሉ ትውልደ አፍሪካውያን አርቲስቶች በመቀጠል ታሪክ ሠርታለች።

የቤኒን ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ታሎን “በአስገራሚ ጉዞዋና በዚህ ስኬቷ ለሁሉም ምሳሌ ትሆናለች” ሲሉ የአርቲስቷን “አስደናቂ ተሰጥኦ እና ታታሪነት” አድንቀዋል።

🏆 በረጅም የሥራ ዘመኗ ዘፋኟ አምስት የግራሚ ሽልማቶችን እና በ2023 የፖላር ሙዚቃ ሽልማትን አሸንፋለች። በአምስት ቋንቋዎች ማለትም የደቡብ ቤኒኑን ፎን፣ ፈረንሳይኛ፣ ዮሩባ፣ ሚና እና እንግሊዝኛ ትናገራለች።

የ64 ዓመቷ አንጀሊክ ኪጆ የዩኔስኮ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር እንዲሁም በአፍሪካ ያሉ ወጣት ሴቶችን የሚያስተምር እና የሚደግፍው የባቶንጋ ፋውንዴሽን መሥራች ናት፡፡ 

“ዎክ ኦፍ ፌም” ከዋክብት የሚደምቁበት ቀን ገና አልተገለጸም፤ ነገር ግን አንድ ነገር እርግጥ ነው፤ ይህም አንጀሊክ ኪጆ ሆሊውድን ማብራቷ ነው!

👉 የሆሊዉድ “ዎክ ኦፍ ፌም” – በሆሊዉድ ኢለቫርድ እና ቫይን ጎዳና ከ2 ሺህ 700 በላይ በቴራዞ እና በነሐስ ኮከቦች ተንቆጥቁጦ የተዘረጋ ታሪካዊ የእገረኞች መንገድ ነው፡፡ የጥብብ ኢንዱስትሪ ሰዎች ላበረከቱት አስተዋፅኦ ክብር የሚሰጥበት ነው፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...