የልብ ጠጋኙ ዶክተር ባስተማራቸው ዩኒቨርሲቲ ተመሰገኑ

Date:

የልብ ቀዶ ጥገና ሐኪሙ እና ከመደበኛ ስራቸው ውጭ ባሻገር ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም አቋቁመው በበጎ ፈቃድ የልብ ህሙማንን በመርዳት የሚታወቁት በጎንደር ዩኒቨርስቱ የተመረቁት ዶ/ር ፈቀደ አጉዋር ጎንደር ዩኒቨርስቲ ለቀድሞ ተማሪዎቹ እውቅና በሰጠበት በዛሬው ዕለት የቀድሞ ምሩቃን (አልሙናይ አዋርድ) ተሸላሚ አድርጓቸዋል።

ዶ/ር ፈቀደ በአንድ ወቅት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ በግልና በቡድን ከ 326 በላይ ቀዶ ጥገናዎችን ማድረጋቸውን መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በልዩ ልዩ መርሐግብሮች 2 ሺ 599 ተማሪዎችን ዛሬ ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም ባስመረቀበት መርሐግብር ላይ በ12 ዘርፎች የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የቀድሞ ምሩቃን በሕዝብ ጥቆማና ምርጫ የዕውቅና ሰርተፊኬት ሰጥቷል።

ከተሸላሚዎች መካከል “ካለን ብናካፍል” የተሰኘ ማዕከል መሥርቶ በርካታ ወገኖቻችንን እየረዳ የሚገኘው ወጣት ዳዊት አየነው ይገኝበታል።

ካለን ብናካፍል የሕጻናት፣ አረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የበጎነት ተግባር የጀመረው በ2010 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ለሕክምና መጥተው አጋዥ የሌላቸውን ህሙማን በመርዳት ነበር።

አንጋፋውና የሠላሙ ዪኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ካስመረቃቸው ተማሪዎችን መካከል 81 ያህሉ የአካል ጉዳተኞች ናቸው።

ድሬቲዩብ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የምክክር ኮሚሽኑ መዝጊያ

የኦሮሚያ ክልል ያቃረበውን ቅሬታ የተመለከተው የአሸማጋይ ቡድን አዲስ አበባ...

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...