የሕይወት እምሻው አዲስ መጽሐፍ ይመረቃል

Date:

47 ታሪኮችን የያዘውና “ዥዋዥዌ” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የደራሲ ሕይወት እምሻው ስድስተኛ መጽሐፍ ሕዳር 6 2018 ዓ.ም ተመርቆ ለንባብ ይበቃል ተብሏል።

ደራሲዋ ስለ አዲሱ መጽሐፏ<< ዥዋዥዌ አርባ ሰባት የዘመን ማስታወሻ ታሪኮችን የያዘ ሲሆን የተስተካከለና የተመሰቃቀለው፤ የተሳካና የተሰናከለው፤ የሚያምርና የሚያስቀይመው፤ የሚያስደስትና የሚያማርረው፤ የሚያኮራና የሚያሳፍረው ዘመነኛ ኢትዮጵያዊ ሕይወታችንን እንደ ወረደ የሰነድኩበት ነው››  ስትል ተናግራለች።

የ “ዥዋዥዌ” መጽሐፍ  ምርቃት ቅዳሜ ህዳር 6 ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ለገሃር በሚገኘው አዲሱ የጃፋር መጽሐፍት መደብር ውስጥ ይከናወናል።

ሕይወት እምሻው ከዚህ በፊት አምስት መፅሐፍትን ማለትም ባርቾ፣ ፍቅፋቂ፣ ማታ ማታ፣ ለእርቃን ሩብ ጉዳይ እና የቡና ቁርስ ለአንባቢያን ያደረሰች ደራሲ ነች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...