የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት መነኮሳትን ለመደገፍ 30 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ ተሰበሰበ

Date:

በተፈጥሮና በሰዉ ሰራሽ አደጋዎች ችግር ላይ ወድቀዉ ለሚገኙት የምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተክህነት የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት መነኮሳት ወደ 30 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡

በገዳሙ ያሉትን መነኮሳት ለመደገፍ በማህበራዊ እና በመገናኛ ብዙሃን በተላለፈ የድጋፍ ጥሪ 29 ሚሊዮን 750ሺህ 620 ብር እና በአይነት ደግሞ 6 ሚሊዮን 208 ሺህ 810 ብር የሚገመት ድጋፍ ማሰባሰብ መቻሉን የገዳሙ የአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ኮሚቴ ክፍል ሃላፊ አቶ ሙሉቀን አሰፋ ተናግረዋል፡፡

በሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የተጀመረዉ ፕሮጀክት 18 ወራት ሞልቶታል ያሉት አቶ ሙሉቀን የፕሮጀክቱን 45 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል፡፡

ከተሰሩት ዋና ዋና ስራዎች መካከል 170 ሜትር ተራራ ተቦርቡሮ ለእናቶችም ለአባቶችም ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ የነበረው ቦታ በአርማታ ደረጃ ተሰርቶለት ለገዳማዊያን እንቅስቃሴ ምቹ እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል።

በአካባቢው ምንም አይነት የመብራት አገልግሎት በላመኖሩ የሶላር መብራት ፣የእናቶች ቤት፣የማዕድ ቤት ፣ለገዳማዊያኑ የእደ-ጥበባት ውጤቶችን ማምረቻ የሼድ ግንባታ፣ የሸማ ስራ ሙያ እንዲሰለጥኑ በማድረግ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ለስራው የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች እና የጥሬ እቃ ግብዓቶችን የማሟላት ስራ ስለ መሰራቱም ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ወራት በተለይ የእናቶችን ችግር ከመቅረፍ በኩል ሰፊ ስራ ተሰርቷል ያሉት ኮሚቴዎቹ ፤ በአባቶች በኩል የቅዱስ ሚካኤል ህንፃ ቤተክርስቲያን ግንባታን ጨምሮ ፣የአባቶች ቤት ግንባታ፣የአብነት፣ዓለማዊ ት/ቤት፣ እና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያ ግንባታ ስራ ለማከናወን ገዳሙ እንቅስቃሴ መጀመሩ ገልጸዋል።

በሁለተኛ ዙር ገዳሙ ለሚያከናዉናቸዉ ፕሮጀክቶች በድምሩ 2መቶ10 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን እነዚህን ስራዎች ከዳር ለማድረስ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚሊኒየም አዳራሽ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በተገኙበት ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ይዘጋጃል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በጎንደር እና በባህር ዳር ከተማዎች ላይ ጉባኤ ይካሄዳልም ነዉ ያሉት፡፡

የገዳሙን እንቅስቃሴ በተመለከተ በዛሬው እለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መቃሪዮስ እና የገዳሙ መነኮሳት እንዲሁም መምህራነ ወንጌል ተገኝተዋል።

መስከረም 14/2018 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...