የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት፤ በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው ከሁለት ሳምንት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት የሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጋዜጠኞች በ50 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የሰጠውን ውሳኔ አፀና።
የሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ አርታኢ ትዕግስት ዘሪሁን እና ሪፖርተር ምንታምር ፀጋው በዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በሰጠው ውሳኔ ላይ የፌዴራሉ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋዜጠኞቹ ከእስር ቢለቀቁ ማስረጃ ሊያጠፉ ይችላሉ በሚል የጠየቀው ይግባኝ ውድቅ ተደርጎበታል።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ተጠርጣሪዎቹ ከእስር ቢለቀቁ ማስረጃ ያጠፉብኛል፣ የሚለውን የፖሊስ ማመልከቻ ባለመቀበል የዋስ መብታቸው እንዲከበር ዛሬ በዋለው ችሎት ወስኖ መዝገቡን መዝጋቱን ሸገር ሬድዮ አስታውቋል።
