ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ጥቃት 17 ሰዎች መገደላቸው ተነገረ፡፡
ጥቃቱ በሀገሪቱ የደቡብ ምስራቅ ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ዘርፈ ብዙ ውድመት እንዳደረሰም ሮይተርስ የአካባቢውን ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ሩሲያ በዲኒፕሮ በፈጸመችው ሁለት ዙር ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች ስለመቁሰላቸው ተሰምቷል፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ የኔቶ አባል ሀገራት ዩክሬን እራሷን እንድትከላከል ወታደራዊ ድጋፍ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ዩክሬንን መደገፍ እና መርዳት መወገን አይደለም ሲሉ በኤክስ የማህበራዊ ትስስር ገጻችው ላይ የጻፉት ዜሌኒስኪ የኔቶ አባል ሀገራት ድጋፋቸው የህይወት አድን ስራ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡
