የሩዝ ምርትን ወደ ገበያ ለማድረስ የመንገድ ችግሮች እየተፈቱ መሆኑ ተገለጸ

Date:

በዘንድሮው ዓመት ከ33 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሩዝ ምርት ይጠበቃል

በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን የሩዝ አምራቾች ምርታቸውን ያለችግር ወደ ገበያ ማድረስ እንዲችሉ የመንገድ መሠረተ ልማት ችግሮችን የመፍታት ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ።

በተለይም በሸቤ ሰምቦ ወረዳ በኪሼ ቀበሌ ከ100 ሄክታር በላይ መሬት ላይ ሩዝ እያለሙ ያሉ አርሶ አደሮችና ባለሀብቶች ያነሱትን የመንገድ ችግር ለመፍታት፣ የመንግሥትን፣ የአርሶ አደሩንና የባለሀብቱን አቅም የማቀናጀት ሥራ መጀመሩን የዞኑ ምክትል የግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚፍታህ ጋሊ ገልጸዋል።

ኃላፊው በዞኑ በዘንድሮው ዓመት ከ33 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሩዝ እንደሚመረት መጠበቁን ጠቁመው፣ የሩዝ ልማት ከቀደሙት ዓመታት አንጻር ከፍተኛ ዕድገት እንዳሳየ አብራርተዋል።

በቀደሙት ዓመታት ሩዝን ከውጭ ስታስገባ የነበረችው ኢትዮጵያ፣ አሁን የሀገር ውስጥ ፍላጎቷን ከማሟላት ባለፈ ምርቷን ወደ ውጭ ገበያ ለማቅረብ ወደሚያስችል ደረጃ እየተሸጋገረች መሆኑም ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ዛሬ ያደረገውን ወሳኝ ጨዋታ 1ለ0 ተሸነፈ !

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የንባብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

የንባብ ባህልን ለማነቃቃት ያለመ 15ኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ፌስቲቫል...

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የኤንሪኮ ማቴይ ሽልማት ተሸለሙ

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በአፍሪካና በአውሮፓ መካከል ያለውን...