የሳንባ ካንሰር

Date:

የሳንባ ካንሰር ምንድን ነው?

የሳንባ ካንሰር ማለት በሳንባ ውስጥ የሚገኙ ህዋሳት ከመደበኛ ዕድገታቸውና ቁጥራቸው ውጪ ጤናማ ባልሆነ መልኩ መባዛት ነው፡፡ የሳንባ ካንሰር ከሳንባ ተነስቶ ወደ አንጎል እንዲሁም ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ሊሰራጭ ይችላል፡፡

የሳንባ ካንሰር ምን ያህል ተስፋፍቶ ይገኛል?

  • የሳንባ ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዛት የሚከሰት ካንሰር ነው፡፡
  • የሳንባ ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ በገዳይነቱ ቀዳሚ ነው፡፡
  • የሳንባ ካንሰር በኢትዮጵያ በወንዶች ዘንድ በብዛት ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች ስድስተኛው ነው፡፡ የተለያዩ አጋላጭ ሁኔታዎች ቢኖሩም ዋነኛው ማጨስ ነው፡፡ ለሳንባ ካንሰር ዋነኛ አጋላጭ ሁኔታ ነው፡፡ የትምባሆ ምርቶችን መጠቀም ለሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ይጨምራል፡፡ በማንኛውም የዕድሜ ክልል ማጨስን ማቆም በሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ሊቀንስ ይችላል፡፡ ደባል አጫሾችም ለሳንባ ካንሰር የተጋለጡ ናቸው፡፡
    ትኩረት ያለማድረግና ያለመረጋጋት ችግር
    በአብዛኛው ልጆች ላይ ሊከሰት የሚችል ስነ አይምሮና ባህሪ እክል ነው። በተለይም ወንድ ልጆች ላይ ይታያል። ይህ እክል ያለባቸው ልጆች ቅብጥብጥ ፤ ትእግስት የሌለው፤ ችኩል ፤ በአጠቃላይ አስቸጋሪ ብለን የምንለውን ባህሪ ያሳያሉ። በተለይም በሀገራችን በዚህ እክል ላይ ያለን እውቀት አናሳ ስለሆነ ወላጆች ብዙ ሲጨነቁና ልጆቻቸውን በተለያዩ ቅጣቶች ሲያስጨንቁ ይስተዋላሉ።
  • በምን ምክንያት ሊከሰት ይችላል?
    ▪ምክንያቱ እንዲህ ነው ተብሎ ባይታወቅም በአለም አቀፍ ጥናት ላይ እንደሚያሳየው ከሆነ ለትምህርት ከደረሱ ህፃናት መካከል ከ5-10 % የሚሆኑት ህፃናት ይህ ችግር ሊታይባቸው ይችላል።
    ኤዲኤችዲ የሥነ ባሕሪ ችግር 2 አይነት አለው
  1. Hyper Active Impulsive ADHD (እረፍት የሌላቸው ወይም ቀዠቃዣ)
    ▪በአንድ ቦታ አርፈው መቀመጥ ይቸግራቸዋል። መንቀሳቀስና መሮጥን ይፈልጋሉ። በአንድ ቦታ ተረጋግቶ ጨዋታን መጫወት አይችሉም።
    ▪ብዙ ያወራሉ፤ በሌሎች ወሬ መሀል ይገባሉ እንዲሁም አላስፈላጊ ንግግሮችን ሊያደሮጉ ይችላሉ።
    ▪ተራቸውን ጠብቀው መናገር ወይም ድርጊቶችን መፈፀም ይቸገራሉ።
  2. Inattentive type ADHD (ትኩረት የሌላቸው)
    ▪በዚህ አይነት ኤዲኤችዲ ያላቸው ልጆች ብዙውን ጊዜ ለትናንሽ ነገሮች ትኩረትን አይሠጡም። በተለይም ከእኩዮቻቸው ጋር ሲስተያዩ በግዴለሽነት ስህተት ሲያደርጉ ይስተዋላሉ።
    ▪ትኩረትን የሚይጠይቁ ስራዋች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት የላቸውም። ሀሳባቸውን መሰብሰብ ላይ ይቸገራሉ።
    ▪እንዲሁም ብዙ ጊዜ ትዕዛዝን ለመተግበር ይቸገራሉ።የትምህረት መሳሪያዎችን ትምህርት ቤት በተደጋጋሚ ረሰተው መምጣት እንደምሳሌነት ሊጠቀስ ይችላል ።
    ▪በቀላሉ ይረበሻሉ (Easily disturbed) ስለዚህም የትምህርት አቀባበላቸው ከሌሎች ዝቅ ሊል ይችላል። አንዳንድ ልጆች የሁለቱም አይነት ምልክት Combined type) ሊታይባቸው ይችላል።
    ሕክምናው ምንድን ነው?
    ▪የሥነልቦና ሕክምና(psychotherapy)
    ▪በልዩ ትምህርት(Special Education)
    ▪የልጆች የአዕምሮ ሐኪም (Child psychiatrist) አይቶ በሚያዛቸው በመድሐኒቶች ከላይ ባሉት አማራጭዎች በመታገዝ የሚስተካከሉና መሻሻል ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ወላጆች፤ አሳዳጊዋች፤ እንዲሁም መምህራን እንዲህ ዓይነት ባሕሪ ያላቸውን ልጆች በአግባቡ ድጋፍና አንክብካቤ በማድረግ ፤በማሳከም ችግራቸውንና የትምህርት አቀባበላቸውን ቀስ በቀስ ማስተካከል ይችላሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኔታንያሁ እና ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ በዋይት ሀውስ እንደሚወያዩ ተገለጸ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፤ ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ...

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ውይይት አካሄደች

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን...

የካፍ ፕሬዝዳንት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ በ24 ተሳታፊ ሀገራት እንደሚካሄድ አስታወቁ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሙትሰፔ የ2027...

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና መስጠት ጀመረ

ሆስፒታሉ በቀን ከ300 በላይ ታካሚዎችን ያስተናግዳል የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ...