የስሙ ትርጓሜ አክሊል እንዲሁም ብርሃን የሚያስገባ መደብ ማለት ነው

Date:

ታላላቆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅዱስ ፓውሎስንና ናትናኤል፣ በሌሊት ወደ ጌታ እየሔደ ይማር የነበረው ኒቆዲሞስንና በርካታ የኦሪት ምሁራንን ያስተማረው ታላቁ የኦሪት መምህር ገማልያል ዘንድ ጠንቅቆ የተማረ ነው፡፡ በሕገ ወንጌል ክርስትና የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ነው፡፡

ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር፡፡ አባቱ ስምዖን እናቱ ማርያም የሚባሉ በብዙዎች ዘንድም ፍጹም እስራኤላዊ የሚባል በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር፡፡

በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5 ላይ ስለእርሱ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ የስሙ ትርጓሜ አክሊል እንዲሁም ውሃ የማያስገባ ብርሃን የሚያስገባ መደብ፣ ወደብ ለሆቴ ማለት ነው በሚል በቅዳሴ ማርያም አንድምታ ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን፤ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ፡፡

ቅዱስ እስጢፋኖስ የነበረበት ወቅት አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲሁን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበርና መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሃ ጥምቀት እየሰበከ ሲመጣ ነገሩን መረመረ፤ ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው ደቀ መዝሙሩ ሆኖ ለ6 ወራት በትጋት አገለግሎታል፡፡

ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ የተደረገውን ታላቅ ተአምር አይቶ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ሲጠይቀው & ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው& በሚል ልኮት ከጌታ ዘንድ ሔዶ ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ተምሯል፤ ጌታም ከ72ቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን ባረገ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ሲባርክ እንደ ወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅስናን፣ ጵጵስናን የተሾመ ነው፡፡

በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ72ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት አልነበረም፡፡ በፍጹም ልቡም በእውቀት ወንጌልን ይሰብክ ነበር፣ በመንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ሰባት ዲያቆናትን ሲመረጡ እርሱ የ6ቱ ዲያቆናት አለቃና የ8ሺው ማሕበረ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆኗል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ “መንፈስ ቅዱስ የሞላበት፣ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረበት እንደሆነ በሐዋ. 6፣5 ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ “ሊቀ ዲያቆናት” ሲባል እንደ ዘመናችን ሳይሆን እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው፡፡

ለአንድ ዓመት ያህል 8ሺውን ማኅበር እየመራ፣ ወንጌል እየሰበከ ሲጋደል ኦሪት “እጠፋ እጠፋ”፣ ወንጌል ደግሞ “እሰፋ እሰፋ” ብትል አይሁድ “ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው” ብለው በማመናቸው አንድም በትምህርቱ ሊገዳደሩት ስላልቻሉ በልደቱ ቀን ጥር አንድ ቀን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡

እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው:: ለሚወግሩት ሰዎች እንደ አምላኩ “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” በማለት ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ወልድን በአብ ቀኝ ተመለከተው፣ ጌታችንም ሰማያዊ አክሊል ላከለት፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ ለቅሶ እያለቀሱ ቀበሩት፡፡

ስለ ክርስቶስ ፍቅር ራሱን አሳልፎ ሰጠ፡፡ ዛሬም ዓለምን የናቁ ገዳማውያንም ጣዕመ ዓለምን ምረረ ገሀነምን ተጸይፈው ስለ ክርስቶስ ፍቅር ሁሉን ትተው በተለያዩ ገዳማት መንነው የስጋና የዓለም ፈተና ይዋጋቸዋል፡፡ በጸሎትና በጾም ተግተውም ድል ያደርጉታል፡፡ በዚህም ጸሎታቸው ኃይልን ያደርጋል፡፡

እኛም ገዳማቸውን ስንደገፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንካፈላለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ሺ ጂምፒንግ ምርጥ መሪ ነው!”- ትራምፕ

አሜሪካና ቻይና ተፎካካሪ ሳይሆኑ አጋርነት ያላቸው ሀገራት ናቸው አሉ...

የአሜሪካ የፀሐይ ብርሃን ኃይል አምራቾች በኢትዮጵያ ላይ የንግድ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቁ

በአሜሪካ የሚገኙ የፀሐይ ብርሃን ኃይል አምራቾች፣ የቻይና ኩባንያዎች የአሜሪካን...

ምርጫ ለሰላም ግንባታ

ግዮን መጽሔት :-ለኢትዮጵያ ሰላም ምርጫ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው።...