የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሳዳት ጀማል ህመም አጋጥሞት ሆስፒታል መግባቱ ታውቋል።
የቀድሞ ግብ ጠባቂው አሁን ላይ ሆስፒታል መተኛቱ ሲገለፅ ህክምናው በሀገር ውስጥ የማይሰጥ በመሆኑ ከሀገር ወጥቶ እንዲታከም እንደተነገረው ተገልጿል።
ስለሆነም ሳዳት ጀማል ህክምናውን ከሀገር ውጪ እንዲያደርግ ለመርዳት እና ህይወቱን ለመታደግ የድጋፍ ጥሪ ቀርቧል።
ድጋፍ ለማድረግ :- የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000126667338 ይጠቀሙ።
