የኬንያው ኬሲቢ ግሩፕ አንድ የኢትዮጵያ ባንክን በከፊል ለመግዛት ንግግር ጀመረ

Date:

​የኬንያው የባንክ ግሩፕ ኬሲቢ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ አንድ የሀገር ውስጥ ባንክን እስከ 40% የሚደርስ ድርሻ ለመግዛት ንግግር መጀመሩን አስታውቋል።

ይህ እርምጃ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የባንክ ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ካደረገ በኋላ፣ ገበያውን ለመቀላቀል ፍላጎት ካሳዩት ቀዳሚ የውጭ ባንኮች አንዱ ያደርገዋል።

የኢትዮጵያ ፓርላማ የውጭ ባንኮች በሀገሪቱ ውስጥ በቅርንጫፍነት፣ በልዩ ቅርንጫፍነት፣ ወይም ደግሞ እስከ 40% የሚደርስ የባንክ ድርሻ በመያዝ እንዲሰሩ የሚያስችል አዋጅ ካጸደቀ በኋላ፣ ኬሲቢ ይህንን አጋጣሚ ለመጠቀም ተንቀሳቅሷል።

የኢትዮጵያ የባንክ ገበያ በአብዛኛው በግዙፉ የመንግስት ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥጥር ስር ያለ ቢሆንም፣ ሰፊ የዕድገት ዕድል አለው የተባለው ኬሲቢ ግን ነባር ባንክን በከፊል ለመግዛት መምረጡ፣ አዲስ ባንክ ከማቋቋም ጋር ተያይዘው የሚመጡትን ወጪዎችና ጊዜን እንደሚቀንስ ተመላክቷል።

በተጨማሪም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ መደበኛ የፋይናንስ አገልግሎት የሚጠቀሙት ሰዎች ቁጥር ዝቅተኛ  በመሆኑ፣ ይህ አካሄድ ወደ ገበያው ለመግባት የሚያስፈልገውን ከፍተኛ ፉክክርና ወጪ ይቀንሳል።

ይህ ግዢ ከተፈጸመ፣ ኬሲቢ በኬንያ ላይ ብቻ ጥገኛ ከመሆን ወጥቶ ትርፉን በተለያዩ የክልል ሀገራት ማሳደግ ያስችለዋል።

ይሁን እንጂ ዘገባዎቹ እንዳመለከቱት ግሩፑ የሀገር ውስጥ ባንክን እስከ 40% የሚደርስ ድርሻ ለመግዛት ንግግር መጀመሩን ቢገልፁም ከየትኛው የፋይናንስ ተቋም ጋር እንደሆነ ግን የተባለ ነበር የለም።

capitalethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...