የተኩስ አቁም እና በኢራን እስራኤል ግጭት ምን ያህል ሰዎች ሞቱ?

Date:

ዛሬ ማከሰኞ ማለዳ ተግባራዊ የሆነ በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተኩስ ማቆም ይፋ ሆኗል። ነገር ግን ሁለቱም ወገኖች የተኩስ አቁሙን በመጣስ እየተካሰሱ ነው። ዛሬ ጠዋት ተኩስ አቁም መደረጉ መገለጹን ጨምሮ አስካሁን ምን ተከሰተ?

* ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ እና በኳታር አማካኝነት የተደረሰውን የተኩስ አቁም በመጣስ በእስራኤል እና በኢራን ላይ ቁጣቸውን ገለጹ

* ትራምፕ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሁለቱም አገራት “የሚያደርጉትን. . . ነገር አያውቁም” ሲሉ ቁጣ በተቀላቀለበት እና መደበኛ ባልሆነ አገላለጽ ወቅሰዋል

* ቀደም ሲል በኢራን የሥርዓት ለውጥ እንዲደረግ ሃሳብ ሲያንሸራሽሩ የቆዩት ትራምፕ፣ ዛሬ ይህንን ሃሳብ እንደማይደግፉት ተናግረዋል

* እስራአል በዛሬው ዕለት ከቴህራን አቅራቢያ ያለ የራዳር ማዕከልን መምታቷን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በስልክ ካወሩ በኋላ የጦር አውሮፕላኖቹ እንዲመለሱ መደረጋቸው ተገልጿል

* የጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ጽህፈት ቤት ኢራን በሚሳዔል ጥቃቶች የተኩስ አቁሙን ሦስት ጊዜ ጥሳላች በማለት ሲከስ፣ ኢራን አስተባብላለች

* ይህ በእንዲህ እንዳለ ለ12 ቀናት በተካሄደው የእስራኤል ጥቃት 606 ሰዎች መገደላቸውን የኢራን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፤ ሌሎች ምንጮች ግን የሞቱት ሰዎች በሁለት እጥፍ ይጨምራል ብለዋል

* የዛሬው ተኩስ አቁም ተግባራዊ ከመሆኑ ቀደም ብሎ ኢራን ቤርሼባ ላይ በፈጸመችው ጥቃት አራት እስራኤላውያን ሲገደሉ፣ በኢራን ጥቃት በአጠቃላይ 28 ሰዎች ተገድለዋል።

BBC Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...