የቴሌግራም ማስጠንቀቂያ

Date:

ቴሌግራም (Telegram) ኦፊሴላዊ ያልሆኑ የቴሌግራም መተግበሪያዎችን (Unofficial Apps) በሚጠቀሙ አካውንቶች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እና ማስጠንቀቂያ መስጠት እንደጀመረ አስታወቀ።

ቴሌግራም ” ኦፊሴላዊ ያልሆኑ የተለያዩ መተግበሪያዎች የሚጠቀሙ ከሆነ የመልዕክት ልውውጡ ደህንነት ሊጠበቅ አይችልም፤ ለአደጋ ሊጋልጥም ” ይችላል ብሏል።

በተለይ በሩሲያ ውስጥ “Telega” የተሰኘ የቴሌግራም መሰል መተግበሪያ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው።

የደህንነት ባለሙያዎች እንደሚሉት፥ ይህ መተግበሪያ የተጠቃሚዎችን አጠቃላይ መልዕክቶች እና መረጃዎች የመጥለፍ አቅም አለው።

ቴሌግራም እነዚህን ኦፊሴላዊ ያልሆኑ መተግበሪያዎች የሚጠቀሙ አካውንቶችን ለይቶ “Flag” እያደረገ (ምልክት እየሰጠ) ይገኛል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኦፊሻል ያልሆነው “Telega” አፕል ከአፕስቶር ላይ አውርዶታል።

ኦፊሴላዊ ያልሆኑ የቴሌግራም መተግበሪያዎች ምንድናቸው ?

እነዚህ መተግበሪያዎች የቴሌግራምን Open Source ኮድ በመጠቀም የተሰሩ ቢሆንም አበልፃጊዎቹ የራሳቸውን ኮዶች ይጨምሩበታል።

ለምሳሌ፦ Nicegram, Telega, Nekogram , Mobogram , Vidogram፣ Nijagram … ሌሎችም እጅግ ብዙ ብዙ አሉ።

እነዚህ ከኦፊሴላዊ ቴሌግራም ውጭ በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የመተግበሪያ አበልጻጊዎች የሚሰሩ ናቸው።

🚨 አንዳንድ ” ቴሌግራም መሰል ” መተግበሪያዎች ምን ያስከትላሉ ? ኦፊሴላዊ ያልሆነውን ቴሌግራም መጠቀም ምን መዘዝ አለው ?

1. የመረጃ ደህንነት ጥሰት ፦ ወደ መተግበሪያዎቹ ሲገባ ዋናው የቴሌግራም አካውንት አክሰስ ይደረጋል ፤ በዚህም የግል የቴሌግራም መረጃዎች አደጋ ላይ ይወድቃሉ።

የተጠቃሚውን እና ቴሌግራም ላይ የተመዘገቡ ስልክ ቁጥሮችን የማግኘት፣ የግል መልዕክቶችን የማንበብ እንዲሁም የኦንላይን ሁኔታቸውን እንዲያውቁት እድል ይሰጣቸዋል።

2. ማልዌር እና ስፓይዌር ፦ 2023 ላይ ባለሙያዎች ጥናት ሲያደርጉ፣ 60000 ስልኮችን በቫይረስ የበከሉ የቴሌግራም አምሳያ መተግበሪያዎች ተገኝተዋል።

ልክ እንደ እውነተኛው ቴሌግራም የሚመስሉ ነገር ግን “ሌቦች የሰሯቸው” መተግበሪያዎች ስልክ ላይ አንዴ ከገቡ በኋላ ፦

👥 በስልክ ላይ የተቀመጡ የሰዎች ስም እና ስልክ ቁጥር በሙሉ ሊወሰዱ ይችላሉ።

💬 ሰዎች የሚጽፏቸውን እና የመጡላቸውን የግል መልዕክቶች በሙሉ እየገለበጡ ይወስዳሉ።

ሚስጥር በሌሎች እጅ ላይ ይወድቃል። ከጀርባ ብዙ ግላዊ መረጃዎች ተጋላጭ ይሆናሉ።

3. አካውንትን ሙሉ በሙሉ መነጠቅ (Account Hijacking) ፦ አንዳንድ መተግበሪያዎች “Trojanized” ናቸው ማለትም ከውጭ ሲታዩ ጠቃሚ ይመስላሉ፣ ውስጣቸው ግን አጥፊ ሶፍትዌር የያዙ ናቸው።

እነዚህ የሶስተኛ ወገን የቴሌግራም መተግበሪያዎች የሰዎችን Session / የመግቢያ ፍቃድ ይሰርቃሉ። በዚህም ምክንያት ፦

– እንደ ሩስያ ፣ ዩክሬን ፣ ኢራን ፣ ሊባኖስ … የመሳሰሉ የጦርነት ቀጠና እንዲሁም የፖለቲካ ውጥረት ባለባቸው ሀገራት ሰዎች ሳያውቁት በግድ የተለያዩ ቻናሎች እና ግሩፖች ውስጥ አባል ይደርጋሉ። በዚህም ሰዎች ያለፍላጎታቸው እንዲገቡ ተደርገው ፕሮፖጋንዳ እና የተለያዩ መልዕክቶች ወደ ስልካቸው እንዲደርሳቸው ይደረጋል። (በግድ ሰዎችን ግሩፕ እና ቻናል ላይ የሚያስገቡት ሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ናቸው)

– ዋናውን የአካውንቱን ባለቤት አስወጥተው / Log out አድርገው አካውንቱን ሙሉ በሙሉ ሊቆጣጠሩት ይችላሉ ፤ ቀጥሎም ለወንጀል እና ማጭበርበር ስራዎች ይውላል።

ሲጠቃለል በተለያዩ ሀገራት የታየው ነገር ፥ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች የቴሌግራም ሚስጥራዊ ኮድ በዋናው መተግበሪያ ፣ በኢሜል፣ ወይም በስልክ እና በSMS ተቀብለው ወደ ኦፊሴላዊ ያልሆኑ መተግበሪያዎች ውስጥ ከገቡ በኋላ ወዲያው ፍቃዳቸውን እንዲያጡት ይሆናል ፤ እንዲሁም ያለ ሰዎቹ ፍቃድ አካውንታቸው እንቅስቃሴ ይደረግበታል።

ቴሌግራም ምን ይላል በዚህ ጉዳይ  ?

የቴሌግራም መስራቹ ፓቬል ዱሮቭ ከዚህ ቀደም ግልጽ አድርገው እንደተናገሩት፥ ቴሌግራም ኦፊሴላዊ ያልሆኑ መተግበሪያዎችን ደህንነት ሊያረጋግጥ አይችልም።

በእነዚህ መተግበሪያዎች አማካኝነት መረጃ ቢሰረቅ ወይም አካውንት ቢጠለፍ ቴሌግራም ምንም ዓይነት ኃላፊነት አይወስድም።

ቴሌግራም ለደህንነት ሲባል ሁሌም ቢሆን  የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎችን ከመጠቀም ይልቅ ዋናውን ቴሌግራም መጠቀም ይመክራል።

⚫ ኦፊሴላዊ ያልሆኑ ቴሌግራሞች በተለይ ጦርነት እና ፖለቲካው በጦዘባቸው አካባቢዎች የሰዎችን መረጃ ለመመንተፍ በስፋት ይውላሉ።

ዋናውና ኦፊሴላዊው ‘ ቴሌግራም ‘ የሚባለው የቱ ነው ? በዚህ ምልክት 📱 የምናገኘው ትክክለኛው፣ እውነተኛውና ህጋዊው የድርጅቱ የቴሌግራም መተግበሪያ ነው።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዳዲስ እና የሁለተኛ ዙር መራጮች አቅምና ሚና

ግዮን መጽሔት :- በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ላይ የአዳዲስ (ለመጀመሪያ...

በ’ፊንቴክ’ የማጭበርበር ወንጀል በተጠረጠሩት ላይ ተጨማሪ ቀጠሮ ተሰጠ

በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ስም በተፈጸመ  የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር...

የጣሊያን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያደረጉት የኢንቨስመንት መጠን 723 ሚሊዮን ዩሮ መድረሱ ተሰማ

ከ20 በላይ የጣሊያን ኩባንያዎች  በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን...

ለ7ኛው ምርጫ 51 ሺህ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸው ተገለጸ

ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 51 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን የኢትዮጵያ...