ለ7ኛው ምርጫ 51 ሺህ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸው ተገለጸ

Date:

ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 51 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ጥምረት አስታውቋል።

የምርጫ ታዛቢ ድርጅቶች ጥምረት ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ኃይለማርያም እንደገለጹት፤ ምርጫውን ለመታዘብ 5 ሺህ ታዛቢዎችን ለማሰማራት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቀዋል።

ከእነዚህም መካከል 522 የሚሆኑት የረዥም ጊዜ ታዛቢዎች ሲሆኑ፣ የምርጫ ጣቢያዎችን የመጎብኘትና የመራጮች ምዝገባ ሂደቱን የመታዘብ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

ታዛቢዎቹ በወረቀት የሚከናወኑ 12 የመራጮች ምዝገባ ጣቢያዎችን እንዲሁም በታብሌት የሚከናወኑ 8 የምዝገባ ጣቢያዎችን በቅርበት እንደሚከታተሉ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

የታዛቢዎቹ የክትትል ሥራ እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፣ በምርጫው ዕለትም ሂደቱን በንቃት እንደሚታዘቡ ታውቋል። ይህም የምርጫውን ተዓማኒነትና ግልጽነት ለማረጋገጥ ዓይነተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

የታዛቢዎችን አቅምና ጥራት ለማረጋገጥ “ዲጂታል ኤሌክሽን ኦብዘርቬሽን ወርክ ስፔስ” የተባለ አዲስ የቴክኖሎጂ ሥርዓት ስራ ላይ መዋሉን አቶ አበራ ጠቁመዋል።

ይህ ቴክኖሎጂ ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ የታዛቢዎች ምልመላና የቁጥጥር ችግሮች ለመፍታት እንዲሁም የጊዜ ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችል ነው ተብሏል።

አዲሱ አሠራር በቀጣዩ ጠቅላላ ምርጫ የታዛቢዎችን የሥራ አፈጻጸም በብቃት ለመቆጣጠር እንደሚያስችል ጥምረቱ ገልጿል።

ለአሐዱ ራዲዮ


ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...