የንቡረ ዕድ በላይ ዕረፍት በማስመልከት አቡነ ማትያስ የኃዘን መልዕክት አስተላለፉ

Date:

የቅዱስነታቸው የኃዘን መግለጫ እንደሚከተለው ይነበባል

ንቡረ ዕድ በላይ መረሳ  ሃይማኖት ያላቸው፣ ሃይማኖትን የመሰከሩ፣ ሃይማኖትም የመሰከረችላቸው፣ ወላዴ አእላፍ፣ መምህረ አሕዛብ፣ ፍቅረ እግዚአብሔርና ፍቅር ቢጽ የጸናላቸው፣ ዘመናቸውን በሙሉ ያስተማሩ፣ ሁሉን በእኩል ዓይን የተመለከቱ፣ ቃለ ወንጌልን በምእመናን ልብ ላይ የዘሩ ታላቅ ገበሬ፣ ፍሬአቸውን በብዙኃን ልጆቻቸው ላይ ያዩ፣ አበ ብዙኃን፣ አንደበታቸው ድንቅፍ የማይልባቸው፣ የዘመን ጎርፍ የማይወስዳቸው፣ በስፍራቸው የተገኙ፣ በትክክል ያወቁ፣ በነጻ የተቀበሉትን በነጻ የሰጡ፣ ተንቀሳቃሽ ቤተ መጻሕፍት ነበሩ።

እኒህ የሁላችን የዘመን እኩያ፣ የትምህርት ቤት ባልንጀራ፣ ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን የሆኑት አባት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የሰማነው በከፍተኛ ኀዘን ውስጥ ነው።

የሕዝባቸውን መከራ በልባቸው ተሸክመው ለኖሩት ለእርሳቸው ይህ ዕረፍት ቢሆንም ለቤተ ክርስቲያን አባቶችና ለምእመናን ግን ትልቅ ጉዳት ነው።

ስለሆነም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅርስ ከመሆናቸው አንጻር የእርሳቸው ኅልፈት  እንደ አንድ ሰው ኅልፈት የሚታይ ባለመሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስና በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም የተሰማንን ኀዘን እንገልጻለን!

በታላቁ ሊቅ ዕረፍት ያዘናችሁ ሁሉ እርሳቸው በሚታወሱበት መልካም ተግባራቸው እና በደቀ መዛሙርቶቻቸው ሕያው ናቸውና ልትጽናኑ ይገባችኋል።

እግዚአብሔር አምላካችን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን። በሕይወተ ሥጋ ለተለዩን ዕረፍተ ነፍስን ፣ በዚህ ለቆየነውም መጽናናትን ይላክልን!

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃን ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ
©የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...