የአለም “ምርጥ የስፖርት ጋዜጠኝነት አመታዊ የሽልማት ፕሮግራም”

Date:

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር የ2027ቱን የዓለም አቀፍ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር (AIPS) አመታዊ ጉባኤን ለማዘጋጀት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አገኝቷል።

ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው በዚህ ጉባኤ ላይ :-

– ከ100 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ተሳታፊ ጋዜጠኞች ይመጣሉ

– የተለያዩ አለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት መሪዎች ይሳተፋሉ

– የአለም “ምርጥ የስፖርት ጋዜጠኝነት አመታዊ የሽልማት ፕሮግራም” ይካሄዳል

– የAIPS Young Reporters ስልጠና ይካሄዳል።

ይህ አለምአቀፍ ኹነት ከስፖርት ዘገባ ባለፈ ለኢትዮጵያ ስፖርት ዲፕሎማሲ፣ ኢኮኖሚ እና ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ፋይዳም እንደሚኖረው ይታመናል።

ይህ ጉባኤ ኢትዮጵያ “የስፖርት ቤተሰቡን” በአንድ ጣሪያ ስር በመሰብሰብ በስፖርቱ ዓለም ያላትን ስም የምታድስበት ትልቅ መድረክ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...