የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚን ጨምሮ ሦስት የጦር መርከቦች በኦማን ባሕረ ሰላጤ አቅራቢያ ታዩ

Date:

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ኢራን ወደቦች የሚጓዙ እና ከወደቦቹ የሚወጡ መርከቦችን እንቅስቃሴ ለማገድ ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ 11 ሰዓት ላይ ተጀምሯል።

ቢቢሲ ቬሪፋይ የሳተላይት ምስሎችን በመጠቀም የፕሬዝዳንቱ እገዳ ምን ሊመስል እንደሚችል ለመረዳት ሲሞክር ቆይቷል።ቅዳሜ ዕለት የተነሱ ሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዩት ግዙፉ የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ‘ዩኤስኤስ አብራሃም ሊንከን’ በኦማን ባሕረ ሰላጤ ምሥራቃዊ ጫፍ በኩል ይገኛል።

ግዙፉ የጦር መርከብ ያለበት ርቀት ከኢራን የባሕር ዳርቻዎች ያለው ርቀት 200 ኪሎ ሜትር ገደማ ነው።የኢራን ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ይህ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ የታጠቀ መርከብ በዚህ ልክ ወደ ባሕረ ሰላጤው ቀርቦ ታይቶ አይታወቅም።

በሳተላይት ምስሉ ላይ የሚታዩት በቅርብ ያሉ ሌሎች መርከቦች ያላቸው ቅርጽ እና ግዝፈት ከአሜሪካ ባሕር ኃይል የሚሳዔል አውዳሚ መርከቦች ጋር ተመሳሳይ ነው።እነዚህ መርከቦች ከአውሮፕላን ጫኙ ‘ዩኤስኤስ አብራሃም ሊንከን’ ጋር በአንድነት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ እንደሆኑ ይገመታል። ይሁን እንጂ ምስሉ ላይ የሚታዩት የትኛዎቹ መርከቦች እንደሆኑ በትክክል መለየት አልተቻለም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...