የአረብ ሀገራት መሪዎች እስራኤል ኢራንን ማጥቃቷን ተከትሎ ውጥረቱ እንዲረግብ ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም በእስራኤል እና ኢራን የተፈጠረውን ግጭት በሁሉም የአረቡ ዓለም የሚገኙ መግስታት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ መፈለግ አለባቸው ተብሏል ፡፡
ቀጠናዊ ውጥረቱን ተከትሎ የሳውዲ አረቢያ፡ ኳታር፤ ግብጽ፡ ዮርዳኖስ፡ ኩዌት ፤ የኢራቅር እና ና ፍልስጤም ባለስልጣናት ባወጡት መግለጫ፤ እስራኤል እና ኢራን ጦር ከመማዘዝ መታቀብ እንዳለባቸው አሳውቀዋል፡፡
የሳውዲው ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማን ለዶናልድ ትራምፕ ስልክ ደውለው በእስራኤል ጥቃት ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ፤ ሁሉም ወገኖች ሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄን መምረጥ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
የሳውዲው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፈይሳል ቢን ፋርሃን ለኢራኑ አቻቸው አባስ አራግቼ ስልክ ደውለው የእስራኤልን ድርጊት ካወገዙ በኋላ ውጥረቱን ማርገብ እንደሚገባ መወያየታቸው አናዶሉ እና የኒ ሳፍክ ኒውስ አስነብበዋል፡፡
