ኢራን አሜሪካንንና አጋሮቿን አስጠነቀቀች

Date:

“ኢራን ሚሳኤሎችን የምታስወነጭፍ ከሆነ ቴህራን ትቃጠላለች” -እስራኤል

እስራኤል የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ፣ ኢራን አጸፋዊ ሚሳኤሎችን ያስወነጨፈችበት የሁለቱ አገራት ፍጥጫ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።

*እስራኤል በድጋሚ አርብ ምሽት በፈጸመችው ጥቃት በርካታ ኢላማዎች መምታቷን አስታውቃለች።

*በቴህራን የመኖሪያ ህንጻ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 20 ህጻናትን ጨምሮ 60 ሰዎች መሞታቸውን የኢራን መንግሥታዊ ሚዲያ ዘግቧል።

*በኢራን አጸፋዊ የሚሳኤል ጥቃቶች ሦስት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል።

*አሜሪካ ወደ ግጭቱ እንድትገባ ከተደረገች ሁኔታዎች የበለጠ ሊያገረሹ ይችላሉ ተብሏል።

*ኢራን ሚሳኤሎችን የምታስወነጭፍ ከሆነ መዲናዋ “ቴህራን ትቃጠላለች” ሲሉ የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር አስጠንቅዋል።

  • የእስራኤል መከላከያ ኃይል ዘጠኝ የኢራን የኒውክሌር ሳይንቲስቶችንና ባለሙያዎችን ገድያለሁ አለ። ጦሩ ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ በፈጸመው ተከታታይ ጥቃት የገደላቸው የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ስድስት ናቸው ብሎ ነበር።

*ኢራን በእስራኤል ላይ እየወሰደች ያለችውን አጸፋዊ እርምጃ ለማስቆም አሜሪካ፣ ፈረንሳይና ዩናይትድ ኪንግደም እስራኤልን የሚያግዙ ከሆነ፣ በቀጣናው የሚገኙ የጦር ሰፈሮቻቸውን ኢላማ እንደምታደርግ ማስጠንቀቋን የኢራን መንግሥታዊ ሚዲያ ዘግቧል።

(ቢቢሲ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...