የታላቁ አርቲስት ደበበ እሸቱ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
የአርቲስት ደበበ እሸቱ ሥርዓተ ቀብር በተመለከተ በብሔራዊ ቴአትር የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴ መግለጫ ሰጥቷል።
አርቲስት ደበበ እሸቱ /ጋሽ ደቤ/ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የኪነ ጥበብ ታሪክ ታላቅ ዐሻራ ያኖረ አርቲስት እንደነበር ተገልጿል።
የታላቁ አርቲስት ስርዓተ ቀብር ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም የተገለጸ ሲሆን ከዚያ በፊት አምስት ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የክብር ሽኝት እንደሚደረግለት ታውቋል።
በኢትዮጵያ ፍቅር የተጠመደ ወዳጆቿን የሚወድ፤ጠላቶቿን አብዝቶ የሚጠላ፤ በስራውና በሙያው የተመሰገነ አርቲስት መሆኑም ተገልጿል።
