ኑ ጥቂት ድጋፍ አድርገን ተስፋ እናለምልም ‼️
ባለ ወርቃማ ድምጹ ትንታጉ አንጋፋ ጋዜጠኛ ወንድማችን በላይ በቀለ በድንገተኛ ህመም በአልጋ ላይ ከዋለ ቀናት ተቆጥረዋል። እጅግ በጣም ትሁትና ሙያውን አኮባሪው ጋዜጠኛ በላይ ከህመሙ ለማገገም የእኛን የሁላችን ድጋፍ ይፈልጋል ተብሎ ከተነገረን ከ15 የቀናት በላይ አልፏል። ከእኛ ከሙያ አጋሮቹ ማለፍ የሌለበት ድጋፍ የህክምና ድጋፍ እስካሁን አላገኘም ። ሌላው ቢቀር ጋዜጠኛው ባገለገለባቸው በኢቢሲ ፣ በኢቢኤስ እና በሰይፉ ሾው ድጋፍ እንዲደረግለት ለምን የድጋፍ ጥሪ ማስተላለፍ አልተቻለም ? እጅግ በጣም ያማል…
አሁንም አልመሸም። ይህን መረጃ የደረሳችሁ በመላ ኢትዮጵያ የምትገኙ ወገኖቼ አነሰ በዛ ሳትሉ ለአንጋፋው ጋዜጠኛ ለበላይ በቀለ የእርዳታ ጥሪ በንግድ ባንክና በጎ ፈንድ ሚ የቻላችሁትን ታደርጉ ዘንድ በፈጣሪ ስም እማጸናችኋሁ 🙏
ጎፈንድሚ (Support Belay Bekele’s Medical Care)
📍የአካውንት ስም፦ የላይ አለማየሁ በፍቃዱ
🏦 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
የአካውንት ቁጥር፦ 1000191873061
♦️በጸሎት፣ በማበረታታትና በምንችለው የገንዘብ ድጋፍ ከጋዜጠኛ በላይ በቀለና ከቤተሰቦቹ ጎን እንቁም ። የአንጋፋውን ጋዜጠኛ ድምጽ እንደገና እንስማ ‼️
📍ኑ ጥቂት ድጋፍ አድርገን ተስፋ እናለምልም
ፈጣሪ ምህረቱን ይላክለት 🙏
ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 11 ቀን 2019 ዓም
