የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ  22 አዲስ ረቂቅ መመሪያዎችን አዘጋጀ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የከተማዋን ፈጣን ዕድገትና የልማት እንቅስቃሴዎች በይበልጥ ለመደገፍ እንዲሁም ወቅቱ የሚጠይቀውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ 22 አዲስ ረቂቅ መመሪያዎችን ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

አሐዱ ሬዲዮ ከቢሮው ባገኘው መረጃ እነዚህ ነባር መመሪያዎች በመንግስት በጀት አዘገጃጀት ፣ በገንዘብ አሰባሰብ ፣ በክፍያ ሒሳብ አያያዝ እና በውስጥ ቁጥጥር ስርዓት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተጠቅሷል።

ሆኖም ቢሮው የተጣለበትን ስልጣንና ኃላፊነት በከፍተኛ ብቃት ለመወጣት እና ዘመናዊ የፋይናንስ አሰራርን ለመዘርጋት አዳዲስ መመሪያዎችን ማዘጋጀት ግድ በመሆኑ 22 ረቂቅ መመሪያዎችን አዘጋጅቶ ለውይይት ማቅረቡ ተገልጻል።

በአዲስ መልክ ከተዘጋጁት 22 ረቂቅ መመሪያዎች መካከል

👉 የዕቃና አገልግሎት ዋጋ መመሪያ

👉 የበጀት አስተዳዳር መመሪያ

👉 የጥሬ ገንዘብ አስተዳዳር መመሪያ

👉 የገንዘብ ክፍያ መመሪያ

👉 የመንግስት ሰራተኞች የዋስትና አሰጣጥ መመሪያ

👉 የሂሳብ አያያዝ መመሪያ

👉 የፋይናንስ ኃላፊነት መመሪያ

👉 የውስጥ ኦዲት መመሪያ

👉 የውስጥ ቁጥጥር ደረጃዎች መመሪያ

👉 የውስጥ ኦዲት አስተዳደር መመሪያ

👉 የርክክብ አፈጻጸም መመሪያ

👉 የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር የጋራ ፑል መመሪያ

👉 የወጪ ቁጠባ መመሪያ

👉 የታክስ ምህረት አፈጻጸም መመሪያ

👉 የፋይናንስ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት መመሪያ

👉 የድጋፍ ሀብት አሰባሰሰብ እና አስተዳደር አፈፃፀም መመሪያ

👉 የመንግስት ፕሮጀክቶች ክትትልና ግምገማ መመሪያ

👉 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ክትትልና ግምገማ መመሪያ

👉 የመንግስት ንብረት አስተዳደር መመሪያ

👉 የመንግስት ንብረት ኦዲት መመሪያ

👉 የፋይናንስ ኃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት የሚጣሉ ቅጣቶች መመሪያ

👉 የመንግስት ድጎማ አሰጣጥ ምደባና አስተዳደር መመሪያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ነባር መመሪያዎችን ለማሻሻልና አዳዲሶቹን ለማጽደቅ የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ጠቁሞ ሰነዶቹን አበልጽጎ ጽድቅ ለማብቃት ከዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ የግብአት ማሰባሰብ እና አስተያየት መስጫ የ 15 ቀና ጊዜ መስጠቱን አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...