የአዲስ አፍሪካ ሪል እስቴት ኤክስፖ የአራት ቀናት ስኬታማ የሥራ ክንውን

Date:

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት አልሚዎች ማኅበር ባለቤትነት እንዲሁም በከተማ መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከፍተኛ ድጋፍ የተዘጋጀው አዲስ አፍሪካ ሪል እስቴት ኤክስፖ 2026 በድምቀት መጠናቀቁን አዘጋጁ ዶክሳ ኢቨንትስ አስታውቋል።

ከሚያዝያ 15 እስከ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም በተካሄደው በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ 28 ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን ጎን ለጎንም የምሥራቅ አፍሪካ የሪል እስቴት ቀጠናዊ ጉባኤ በኢሌሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል በታላቅ ስኬት ተካሂዷል።

ከእነዚህ ኩነቶች በተጨማሪ ከኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ እና ናይጄሪያ የመጡ የዘርፉ አልሚዎችና ተመራማሪዎች የአዲስ አበባን ዕድገትና ለኢንቨስትመንት ያለውን ምቹነት እንዲገነዘቡ ተደርጓል።

ለዚህም የኮሪደር ልማት ሥራዎችን፣ የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶችንና ታሪካዊ ስፍራዎችን እንዲጎበኙ መደረጉን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

ይህ መርሃ ግብር ኢትዮጵያን የአፍሪካ የሪል እስቴትና የኢንቨስትመንት ማዕከል፣ አዲስ አበባን ደግሞ የቱሪስቶችና የባለሀብቶች መዳረሻ ለማድረግ እንደ መነሻ እንደሚሆን ታምኖበታል።

በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውና በባለድርሻ አካላት ቅንጅት የተካሄደው ይህ አህጉራዊ ትስስርን ያለመ ኤክስፖ በየዓመቱ የሚቀጥል ሲሆን ለዘርፉ ዕድገትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሪል እስቴት አልሚዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ ከተማና የቦርድ አመራሮች በተገኙበት ለእንግዶቹ የራት ግብዣ የተደረገላቸው ሲሆን አገራቸውን እንዲያስታውሱ የሚያደርጉ ባህላዊ ስጦታዎችም ተበርክቶላቸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከፍተኛ የግብር ክፍያ በሕጋዊ ነጋዴው ላይ በመጫን ሲፈጽሙት …

መንግስት ከግብር የሚያገኘው ገቢ የቀነሰው ወይም ከሀገር ውስጥ አጠቃላይ...

ሆስፒታሊቲ እና ቱሪዝም እውቅና እና ሽልማት መርሃ-ግብር ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበር ሁለተኛውን የሆስፒታሊቲ...

ቴህራን ወሽመጡ ወዲያውኑ እንደማይከፈት አስጠነቀቀች

ኦማን ከኢራን ጋር በሆርሙዝ ወሽመጥ ዙሪያ የምታደርገው ንግግር በጥሩ...

ከታክስ በፊት ከ1.54 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ስኬት ባንክ አስታወቀ

​ስኬት ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 4.1 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ...