የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት “አደራ” የተሰኘ የዲጂታል የጥቆማ መድረክ ይፋ አደረገ

Date:

በአፍሪካ ግዙፍ ከሆኑ የሉዓላዊ ሀብት ፈንድ አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ)፣ በሚያስተዳድራቸው የመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ለመታገል ያለውን ቁርጠኝነት ገለጸ።

ሆልዲንግሱ ይህንን ተግባር በዘመናዊ መንገድ ለመፈጸም የሚያስችለውን “አደራ” (Adera) የተሰኘ የዲጂታል ጥቆማ መቀበያ ድረ-ገጽ እና መተግበሪያ በይፋ ስራ አስጀምሯል።

ይህ አዲስ መተግበሪያ በልማት ድርጅቶች ውስጥ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን ለማስፈን ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል። በዚህ መሰረት ማንኛውም ግለሰብ—ሰራተኛ፣ ደንበኛ ወይም ተመልካች—ባለበት ቦታ ሆኖ በድርጅቶቹ ውስጥ የሚፈጸሙ ህገ-ወጥ ተግባራትን በምስጢር እና በታማኝነት መጠቆም እንዲችል ታስቦ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

ይህም ሆልዲንግሱ በሚያስተዳድራቸው እንደ ኢነርጂ፣ ሎጅስቲክስ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን እና ማኑፋክቸሪንግ ባሉ ወሳኝ ዘርፎች የተሰማሩ ከ40 በላይ ግዙፍ ኩባንያዎችን ይጨምራል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል መድረኩን አስመልክተው ሲናገሩ “ይህ ‘አደራ’ የተሰኘው የመረጃ መለዋወጫ መድረክ ተጠያቂነትን ለማስፈን እና የሀገራዊ ኢንቨስትመንቶቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ወሳኝ እርምጃ ነው።

በቁጥጥራችን ስር ያሉ ሁሉም ስራዎች ከፍተኛውን የህግ እና የስነ-ምግባር ደረጃ የተከተሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኞች ነን” ብለዋል።

ይህ ተነሳሽነት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሙስናን ለመዋጋት ለተያዘው እቅድ ትልቅ እገዛ የሚያደርግ ሲሆን፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ያላቸውን ድርሻ በብቃት እንዲወጡ ያስችላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...