ምሁር ችግር ፈቺና መፍትሄ አሳሽ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምሁር ችግር ፈቺና መፍትሄ አሳሽ ነው አሉ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዩኒቨርሲቲው 75ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ “የምሁራን ሚና ለሀገራዊ ብልጽግና” በሚል ርዕስ የጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ምሁር በስሜታዊነት የሚነዳ ሰው አይደለም ብለዋል።
ሐሳብ አክባሪ እና አፍቃሪ፤ ጥልቅ አሰላሳይ እና ብዙ ጠያቂ፤ አንባቢ፣ ነቃሽና ተንታኝነት የምሁር መገለጫዎች እንደሆኑ አስገንዝበዋል።

እንዲሁም ችግር ፈቺና መፍትሄ አሳሽነት የምሁር መገለጫ መሆኑን በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...